የባስኬቶ ዞን ላስካ ዙሪያ ወረዳ ህዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ አመት የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል
የዙሪያ ወረዳው ህዝብ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ካሳሁን ቆሶ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫና የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላን በስኬት ባጠናቀቀችበት ማግስት የሚካሄድ ጉባኤ መሆኑ ልዩ የሚያደርገው መሆኑን ገልጸዋል።
ምክር ቤቱ ያለፈውን መደበኛ ቃለ ጉባኤ፣ ምክር ቤቱ በ2018 በጀት አፈጻጸም ዙሪያ ሐሳብ አስተያየት ሰጥቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
የምክር ቤቱ የ2019 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ እንዲሁም ማስፈጸሚያ በጀት ለአባላቱ ቀርቦ አስተያየት ተሰጥቶበት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።
የላስካ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተመሥገን አዘነ፤ የአስተዳደር ምክር ቤቱን የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።
ዋና አስተዳዳሪው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጉዳዮች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የላስካ ዙሪያ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አይናለም መኮንን የፍርድ ቤቱን የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም፣ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድና የ2019 በጀት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
ምክር ቤቱ የዙሪያ ወረዳውን የፍርድ ቤት የ2019 በጀት 6 ሚሊዮን 967 ሺህ 519 ብር እንዲሆን አፅድቋል።
ዘጋቢ: አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
ጥራቱ የተጠበቀ ከ500 ቶን በላይ እሸት ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
አዲሱ የካቢኔ ስብጥር ኢትዮጵያ የሁሉም መሆኗን በተግባር ያሳየ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
ዕጩ የካቢኔ አባላት ከወትሮ በተለየ መንገድ ባለዕዳና ከፍተኛ አደራ የተጣለባቸው መሆኑን እንዲገነዘቡ ማሳሰብ እወዳለሁ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)