የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት የትምህርት ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ግምገማ እና የ2019 ዓ.ም የተማሪዎች ቅበላ የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ፡ ነሐሴ 06/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት የትምህርት ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ግምገማና የ2019 ዓ.ም የተማሪዎች ቅበላ ንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወልደማርያም እንደገለፁት፤ ባለፉት ሁለት ወራት ምቹ የትምህርት አካባቢ ከመፍጠር አኳያ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት እና በዞኑ እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናት ወደ ትምህርት ቤት የማስገባት ጉዳይ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡
በተለይም በዞኑ በ2019 ዓ.ም በቅድመ አንደኛ እና በመደበኛ ትምህርት ከ2 መቶ 25 ሺ በላይ ተማሪዎች ተመዝግበው ትምህርታቸውን ይከታተላሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲሉም አመላክተዋል።
በዞኑ ከነሐሴ 11 እስከ 30 በሚካሄደው የተማሪዎች ምዝገባ በጊዜ በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ በስኬት እንዲጠናቀቅ የትምህርት አመራሩ እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።
በመድረኩ የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ፣ የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ናስር ሃሰን እና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎችም ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ እርካብነሽ ወ/ማርቆስ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
የዳውሮ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ ሥራ ዘመን 29ኛ መደበኛ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ
የህግ ታራሚዎችን አምራች ዜጋ ለማድረግ የስነ-ልቦና ድጋፍና የክህሎት ማጎልበቻ ስራዎች ወሳኝ መሆናቸው ተገለጸ
የባስኬቶ ዞን ላስካ ዙሪያ ወረዳ ህዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ አመት የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል