የዳውሮ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ ሥራ ዘመን 29ኛ መደበኛ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባዔ አቶ ዳዊት ሚኖታ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በታሪኳ በሃሳብ ልዕልና ላይ ለመመሥረት ሀገራዊ ምክክር እያካሄደች ባለችበት ወቅት መካሄዱ ጉባዔውን ልዩ ያደርገዋል።
ምክር ቤቶች የዲሞክራሲ ተቋማትና የህዝብ ሉዓላዊነት መገለጫ መሆናቸውን ያመለከቱት ዋና አፈ ጉባዔው፤ ተቋማቱ ቀጥተኛ የህዝብ ውክልና የሚንጸባረቅባቸው መድረኮች መሆናቸውን አብራርተዋል።
ምክር ቤቱ በቆይታው፤ የዞኑን ምክር ቤት፣ የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶችን እና የዞኑን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ላይ ተወያይቶ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የ2019 የበጀት ረቂቅ እና የእሰራ ባሌ ከተማ አስተዳደር አዲስ የቀበሌ መዋቅር ቀርበው እንደሚጸድቁም ተመላክቷል፡፡
ዘጋቢ፡ እሸቱ ወርቅነህ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
ጥራቱ የተጠበቀ ከ500 ቶን በላይ እሸት ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
አዲሱ የካቢኔ ስብጥር ኢትዮጵያ የሁሉም መሆኗን በተግባር ያሳየ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
ዕጩ የካቢኔ አባላት ከወትሮ በተለየ መንገድ ባለዕዳና ከፍተኛ አደራ የተጣለባቸው መሆኑን እንዲገነዘቡ ማሳሰብ እወዳለሁ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)