ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳ የተሠራውን 40 ኪሎ ሜትር መንገድ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ
ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 22/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳ የተሠራውን ከሰንገጢ – ጩርጩራ 40 ኪሎ ሜትር መንገድ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
በመንገዱ ግንባታ 2 ድልድዮች የተካተቱ ሲሆን አጠቃላይ በአንድ መቶ አስራ ስምንት ሚሊየን ብር ወጪ የተሠራ ፕሮጀክት መሆኑ ተገልጿል።
5 ቀበሌያትን አቋርጦ የሚያልፈው ይህ መንገድ በገጠር መንገድ ታርጫ ዲስትሪክት የተሠራ መሆኑም ተጠቁሟል።
መንገዱ የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ መዳረሻ ሲሆን አቋርጦ የሚያልፍባቸው አካባቢዎችም በርካታ የግብርና ምርቶች ያሉበት እንደሆነ ተመላክቷል።
አርሶ አደሮች በአካባቢው ያሉ የግብርና ምርቶችን ለማዕከላዊ ገበያ ለማድረስ የመንገዱ ግንባታ ከፍተኛ አበርክቶ እንዳለው ተጠቅሷል።
በመርሃ-ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ መሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የመንገድና ትራንስፖርት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒን ጨምሮ ከፍተኛ የክልልና የዞን አመራሮች እንዲሁም የአካባቢ ማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ዮሐንስ መካሻ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
ምክር ቤቱ በ2018 በጀት አመት ሪፖርት እና የ2019 ጠቋሚ እቅድ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ
በበጀት አመቱ ከ26 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
በበጀት ዓመቱ ከ379 ሺ በላይ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)