የግብርና ምርት ላይ የሚደረጉ ህገወጥ የዋጋ ጭማሪዎችን ለመከላከልና ለማረም ሸማቾች ከመንግስት ጋር በቅንጅት ሊስራ እንደሚገባ ተገለጸ

የግብርና ምርት ላይ የሚደረጉ ህገወጥ የዋጋ ጭማሪዎችን ለመከላከልና ለማረም ሸማቾች ከመንግስት ጋር በቅንጅት ሊስራ እንደሚገባ ተገለጸ

የጂንካ ከተማ አሰተዳደር የሚቀርቡ የግብርና ምርት ላይ የሚደረጉ ህገወጥ የዋጋ ጭማሪዎችን ለመከላከልና ለማረም ሸማቾች ከመንግስት ጋር በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ አመላክቷል።‎

“ደህንነቱ የተጠበቀ ምርትና በራሱ የሚተማመን ንቁ ሸማች” በሚል መሪ ቃል የጂንካ ከተማ አስተዳደር ንግድና እንዱስትሪ ልማት በዓለም ለ43ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ13ኛ ጊዜ በኣሪ ዞንና በጂንካ ከተማ ለ2ኛ ጊዜ የሸማቾች ቀን በዓል ተከብሯል።‎

‎በበዓሉ አከባበር ላይ በከተማው በልዩ ልዩ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት፣ የሚመለከታቸው የዞንና የከተማው አስተዳዳር የአመራር አካላት ባለሙያዎች እና ተጋባዥ እንዶች ተገኝቷል።‎

‎በዕለቱ ለተሳታፊዎች በንግድ ህጎችና አዋጆች ላይ በከተማ አስተዳደሩ ንግድና እንዱስትሪ ልማት ፅ/ቤት ንግድ ኢንስፔክሽንና ሬጉለሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ዳዊት ይርካዮ አማካይነት ሰነድ ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል።‎

‎በመድረኩ ከተሳተፉ የንግዱ ማህበረሰብ አበላት የጂንካ አዲሱ ቅዳሜ ገበያ ቦታ ለንግድ እንቅስቃሴ ምቹ አለመሆን የጫኝና አውራጅ ሠራተኞች የጉልበት ዋጋ ከፍተኛ መሆን የናፍጣና የቤንዚል ህገ ወጥ ንግድ መስፋፋት ጋር ተያይዞ የመንግስት አካላት የቁጥጥር መላላትና ህገወጥ ንግድ የሚያካሂዱ ነጋዴዎች ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች መላላትና አንዳንድ አድሎአዊ አሠራሮች እንደሚስተዋል ከተሳተፊዎች ተነስቷል።‎

‎የጂንካ ከተማ አስተዳደር ንግድንና ኢንዱስትሪ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ሀዚሚ በሰጡት ምላሽ ህገወጥ የነዳጅ ንግድ እንቅስቃሴና ሌሎች ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ህገወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የሁሉም አካላት ትብብር የሚፈለግ በመሆኑ ነጋዴዉ ማህበረሰብ ህገወጦችን ለተቋሙ እንዲጠቁሙና በአጠቃላይ ምክንያታዊ ያልሆነ የተጋነነ ዋጋ ከመጨመር ሊቆጠቡ ይገባል ብለዋል።‎

‎የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ደግፌ ጌታቸው መድረኩን በመሩበት ወቅት አንዳሉት፥ የቀድሞ የጂንካ ቅዳሜ ገበያ በተለይ የአከባቢ ምርት አቅራቢ አርሶ አደሮች ምርታቸውን በተሳለጠ ሁኔታ አንዲያቀርቡ የማያመች በመሆኑ የተደረገ የቦታ ቅያሪ መኖሩን ጠቁመዉ፥ በአዲሱ የግብይት ቦታ ያልተሟሉ የመብራት፣ የፀጥታና ሌሎች ስራዎች በቅርቡ እንደሚመቻቹና ለሸማቾች የሚቀርቡ የግብርና ምርት ላይ የሚደረጉ ህገወጥ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላትን ለማረም በጋራ እንዲሰሩ አሳስበዋል።‎

‎ዘጋቢ: ዳኛቸዉ ደሴ – ከጂንካ ጣቢያችን