ባንኩ አዳዲስ የዲጂታል አገልግሎቶች መጀመሩን አስታወቀ
አዳዲስ ዲጂታል አገልግሎቶችን ማቅረቡን የዳሽን ባንክ አስታውቋል፡፡
ባንኩ ከዓለም አቀፍ የባንክ ተቋማት ጋር በመተባበርም የተለያዩ ዓለም አቀፍ ክፍያዎችን መክፈል የሚያስችል አገልግሎት መስጠት መጀመሩንም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው የማስተዋወቂያ መርሐ-ግብር ላይ ተገልጿል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ኘሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አየለ አዳቶ፣ የተማሪዎች አገልግሎት ዲን አማሎ ሶጋ(ዶ/ር)፣ የሀዋሳ ዳሽን ባንክ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ቢዝነስ ዳይሬክተር አቶ አስናቀ ደምሴ፣ የዳሽን ባንክ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች እንዲሁም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ካውንስል እና የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ተገኝተዋል፡፡
ዘጋቢ፡ መዝሙረ ዳዊት

More Stories
የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ በመንገድ መሠረተ ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሰኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አሰታወቀ
ሳውላ ከተማን ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ምቹ የማድረግ የ5 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ እየተካሄደ ነው
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቱሪዝም ሀብቶችን በማልማትና ሰላምን በማጽናት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል