ባለፉት 8 የለውጥ ዓመታት የህዝቡንና የሀገሪቱን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሳው (ዶ/ር) ገለፁ
”ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ቃል በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ የለውጥ ጉዞ 8ኛ ዓመት አስመልክቶ እና በለውጡ መንግስት የተመዘገቡ ስኬቶችን ዕውቅና የሚሰጥ ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
በድጋፍ ሰልፉ መልዕክት ያስተላለፉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) ፤ በለውጡ መንግስት መሪነት ባለፉት ስምንት ዓመታት በክልላችን ብሎም በሀገራችን የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ታላላቅ ስኬቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።
ባለፉት ረጅም ዓመታት በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ የተቃኙ ስርዓቶች አለመገንባታቸውና ነባሩን አፍርሶ ከዜሮ መጀመር በመሆኑ ይህም የሀገሪቱን ዕድገት ጎድቷል ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ።
ሆኖም ባለፉት 8 ዓመታት በኢትዮጵያ የተጀመረው አዲስ የዲሞክራሲ ልምምድ የነበሩ ቁርሾዎችን በማስወገድ ለዜጎች የተሻለች ኢትዮጵያን ለማስረከብ ምቹ መደላድል መፍጠሩን ዶ/ር እንዳሻው አክለዋል።
በዲሞክራሲ ግንባታ፣ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ እና በዲፕሎማሲ እንዲሁም በማህበራዊ ጉዳዮች ታላላቅ ድሎች የተመዘገቡ በመሆናቸው እነዚህም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል።
በሀዲያ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ታምራት ግዛው በበኩላቸው፤ የድጋፉ ሰልፉ ባለፉት 8 ዓመታት በሀገሪቱ፣ በክልሉ እና በዞኑ የተከናውኑ ስኬቶች የተዘከሩበት መሆኑን ገልጸው መጪው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ፍትሃዊ እንዲሆን ለማስቻል ያለመ ነው ብለዋል።
የዞኑ ህዝብ የሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ያገኘበት ፣ በግብርና፣ በመሰረተ ልማት፣ በከተማ ልማትና በሌሎች አመርቂ ስኬቶች የተመዘገበበት ነው ብለዋል ኃላፊው።
በመሆኑም መጪው ጠቅላላ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ እና ተዓማኒ እንዲሆን ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
በድጋፉ ሰልፉ የተሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት፤ በመደመር ዕሳቤ ባለፉት 8 ዓመታት የህዝቡን እና የሀገሪቱን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን አስታውሰው እነዚህም ሀገራዊ አንድነት የፈጠሩ ናቸው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በዲሞክራሲ ስርዓት ልምምድ ላይ ትገኛለች ያሉት አስተያየት ሰጪዎች፤ በመሆኑም በግንቦት ወር የሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ ተካሄዶ እስኪጠናቀቅ የበኩላቸውን ሀገራዊ ግዴታ እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
በመድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የክልሉ መንግሥት ዋና ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ(ዶ/ር)፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወ/ሚካኤል፣ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አንዮ፣ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሽጉጤን ጨምሮ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳዎች ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ: ሄኖስ ካሳ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
በሆሣዕና ከተማ የሚገነቡ ሆቴሎች የከተማውን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ከተማው ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን የሚያደርግ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ(ዶ/ር) ገለፁ
በደቡብ ኦሞ ዞን በሣላማጎ ወረዳ በሌማት ትሩፋት በቆላማ አካባቢ የኑሮ ማሻሻያ ኘሮጀክት ድጋፍ በዶሮ እርባታ ልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን አርሶ አደሮች ተናገሩ
በጎፋ ዞን ከ950 ቶን በላይ የብረት ማዕድን ክምችት መኖሩ ተገለጸ