በክልሉ ከቱሪዝሙ ዘርፍ ባለፉት 9 ወራት 925.6 ሚሊዮን ብር ተገኝቷል
ባለፉት 9 ወራት 925.6 ሚሊዮን ብር መገኘቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለፀ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊው አቶ ኃይለማርያም ተስፋዬ በሰጡት መግለጫ በበጀት ዓመቱ 33 ሺ 800 የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ክልሉን ጎብኝተው 364 ሚሊዮን ብር ገቢ መገኘቱ ገልፀዋል፡፡
በአጠቃላይ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ቱሪሰቶች ባለፉት 9 ወራት 925.6 ሚሊዮን ብር መገኘቱንም ኃላፊው አብራርተዋል።
ክልሉ ያለው ሰው ሰራሽ፣ ተፈጥሯዊና ባህላዊ አቅሞች ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆን እንዳደረገው ገልፀዋል፡፡
የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ አሁን ላይ ለመሰረተ ልማት ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን አቶ ኃይለማርያም በመግለጫቸው አመላክተዋል።
በቀጣይም ዘርፉን የበለጠ ለማጠናከር የክልሉ መንግስት ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረ ስለመሆኑ አብራርተዋል።
ዘጋቢ፡ ባዬ በልስቲ

More Stories
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
መስቀል የድህነት ምልክት መሆኑን የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል ተናገሩ