እየተካሔደ ያለው ሀገራዊ ምክክር በሀገሪቱ አንድነት እና ሠላም ለማስፈን ፋይዳው የጎላ መሆኑን የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ
የሰላምና የመግባባት ባህል የሰፈነባት፣ ልዩነቶች በውይይት የሚፈቱባት እና ዜጎቿ በሀገራቸው የጋራ እጣ ፈንታ ላይ የሚተማመኑባት ኢትዮጵያን እንደሚጠብቁም ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የሀገሪቱን የቆዩ ልዩነቶችና አለመግባባቶችን በመፍታት በዜጎች ሕይወትና በሀገሪቱ የፖለቲካ ባህል ተጨባጭ ለውጥ እንደሚያመጣ አንዳንድ የከተማው ነዋሪዎች እምነታቸው እንደሆነ ተናግረዋል።
ሀገራዊ ምክክሩ ከልዩነት ወደ መግባባት፣ ከግጭት ወደ ዘላቂ ሰላም እና ከመከፋፈል ወደ ጋራ ሀገራዊ እሴት የሚያሸጋግር መሠረት እንደሚጥል ገልፀዋል፡፡
ምክክሩ የኢትዮጵያን ታላቅነት ከማስቀጠሉም ባሻገር ለዜጎቿ ብሩህ ተስፋ ይዞ ይመጣል ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ ጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ከማተኮር ይልቅ የጋራ በሆኑና በሚያግባቡ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት መስጠት እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡
የምንፈልጋት የተሻለች ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ ለማስረከብና “ችግሮቻችንን በኃይል ሳይሆን በውይይት እንፈታለን” የሚል በውይይት የሚያምን ትውልድ ለመገንባት እንደሚያግዝም አረጋግጠዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ተነሳ ተረፈ – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን

More Stories
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄዎች በዘላቂነት እንዲመለሱ ከየትኛውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኧሌ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ገለፀ
መንግስት የደን ጭፍጨፋን በመከላከል የአየር ሚዛንን ለመጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ እስታውቀ
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ እንዲያስችል ዞኑ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ