የፒኤስጂው ኮከብ ኪቪቻ ክቫራትስኬሊያ አዲስ ወኪል መረጠ!

የፒኤስጂው ኮከብ ኪቪቻ ክቫራትስኬሊያ አዲስ ወኪል መረጠ!

የፓሪስ ሴንት ዠርሜን እና የጆርጂያ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች የሆነው ክቪቻ ክቫራትስኬሊያ ከቀድሞ ወኪሉ ማሙካ ጁጌሊ ጋር ከተለያየ በኋላ አዲስ ወኪል መቅጠሩ ታውቋል።

ክቫራትስኬሊያ ከባድ ድርድሮችን በማካሄድ ከሚታወቀው ፈረንሳዊ ወኪል ሙሳ ሲሶኮ ጋር አብሮ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሷል።

ሙሳ ሲሶኮ የበርካታ ታዋቂ እግር ኳስ ተጫዋቾች ወኪል ነው።

ከእነዚህም መካከል የፒኤስጂዎቹ ኡስማን ዴምቤሌብራድሊ ባርኮላዴዚሬ ዱኤ እንዲሁም ዳዮት ኡፓሜካኖ ይገኙበታል።

ክቫራትስኬሊያ አዲስ ወኪል መምረጡ በፒኤስጂ ቤት የረጅም ጊዜ ኮንትራት ለማደስ እና የተሻለ ደመወዝ ለመጠየቅ ወይም ወደ ሌሎች አውሮፓ ታላላቅ ክለቦች ለሚደረግ ዝውውር መንገድ ለማመቻቸት እንደሆነ እየተገመተ ይገኛል።

ሲሶኮ በፒኤስጂ ስብስብ ውስጥ በርካታ ተጫዋቾችን የሚያስተዳድር በመሆኑ በክለቡ የውል ድርድር እና የዝውውር ፖሊሲ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዳለው ይታወቃል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ