የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በጋሞ ዞን በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
5መቶሺ ብር ግምት ያለው የቁሳቁስ ድጋፍም ለዞኑ አበርክቷል
ሀዋሳ፡ መጋቢት 12/2018(ደሬቴድ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በጋሞ ዞን በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አደረገ።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ድጋፋን ለጋሞ ዞን አስተዳደር አስረክበዋል።
የተከሰተው አደጋ እጅግ ልብ ሰባሪ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉ ህዝብና መንግስት ለተጎጂዎች መፅናናትን ይመኛል ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩና ልዑካቸው የ 5 ሚሊዮን ጥሬ ገንዘብና 5 መቶ ሺ ብር ግምት ያለው ደራሽ ቁሳቁስ ለዞኑ አስተዳደር አስረክበዋል።
የክልሉ መንግስተና ህዝብ ተፈናቃዮችን በማቋቋሙ ሂደት አብሮነቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በአደጋው ለተጎዱ ወገኖች በሁሉም አቅጣጫ እየተደረገ ያለውን ርብርብ አድንቀው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።
አደጋው ከፍ ያለ ጉዳት በማስከተሉ ድጋፉ ተጠናክሮ መቀጠል አለበትም ብለዋል፡፡
ዘጋቢ:-ባዬ በልስቲ

More Stories
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
መስቀል የድህነት ምልክት መሆኑን የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል ተናገሩ