መንግስት የደን ጭፍጨፋን በመከላከል የአየር ሚዛንን ለመጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ እስታውቀ

መንግስት የደን ጭፍጨፋን በመከላከል የአየር ሚዛንን ለመጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ እስታውቀ

ቢሮው ይህንን ያስታወቀው፤ “Harness” የተሰኘ ፕሮጀክት የማስጀመሪያ መድረክ በሚዛን አማን በተካሄደበት ወቅት ነው።

በማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር አስራት ገብረማርያም (ዶ/ር)፤ መንግስት ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ ከሚያደርገው ጥረት ባሻገር መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ ይህንን በጎ ተግባር ዓላማው ማድረጉን አንስተው፤ ግቡን እንዲያሳካ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅት ያስፈልጋል ብለዋል።

የፋርም አፍሪካ ማናጀር አቶ ፈይሳ አሰፋ፤ ፕሮጀክቱ የደን መጨፍጨፍን ለመከላከል ወደ 1 ቢሊየን ብር መድቦ በኦሮሚያ ክልልና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በ11 ወረዳዎች ተግባራቱን እያከናወነ መሆኑን አመላክተዋል።

እነዚህ አካባቢዎች የተፈጥሮ ብዘሃ-ህይወት መናኽሪያ ናቸው ያሉት አቶ ፈይሳ፤ ፕሮጅክቱ ከ228 ሺ ሄክታር በላይ ማሳ ላይ የጥበቃ ስራዎችን እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

በሚቀጥሉት ሦሥት ዓመታት ከ370 ሺ በላይ የሚሆኑ ኑሯቸውን ደን ላይ የመሠረቱ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።

በናቡ ኢትዮጵያ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አስተባባሪ አቶ አሳየ ዓለማየሁ፤ ለፕሮጀክቱ ስኬት የመንግስት ባለድርሻ አካላት ልዩ ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ አስተያየት ሰጥተዋል።

በማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ ላይ የፋርም አፍሪካ አስተባባሪዎችን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ እካላት ተሳትፈዋል።

ዘጋቢ፡ መቅደስ ታደሰ – ከቦንጋ ጣቢያችን