የቤንች ሸኮ ዞን ለሱማሌ ክልል ከ20ሺ በላይ የተለያዩ ዝርያ ያላቸውን የደን ችግኞች በስጦታ አበረከተ
በዞኑ በሐምሌ 10 በአንድ ጀንበር 10 ሚሊየን ችግኝ እንደሚተከልም ተጠቁሟል።
በዞኑ ግብርና መምሪያ የተፈጥሮ ደን እና አከባቢ ጥበቃ ዘርፍ አስተባባሪ እና ምክትል መምሪያ ኃላፊ አቶ ጎጁ ኮይሳ እንደ ሀገር በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ከተያዘው እቅድ ውስጥም በቤንች ሸኮ ዞን ብቻ 10 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል መታቀዱን የተናገሩት ኃላፊው እስካሁንም 6 ሚሊየን 6 መቶ ሺ ጉድጓዶች መዘጋጀታቸውን ጠቁመው 135 ሺ 392 የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ እንደሚሆኑም ተናግረዋል።
ተግባሩንም ለማስፈጸም በሁሉም አደረጃጀቶች ተገቢውን ቅስቀሳ መደረጉን እና ተከላውም 164 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት እንደሚሸፍንም ገልጸዋል።
የሚተከሉ ችግኞች ከመደበኛ የደኝ ችግኝ ባለፈም ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የፍራፍሬ ችግኞችም እንደሚተከሉም ተናግረዋል።
ዞኑ ከ20 ሺ በላይ የተለያዩ ዝርያ ያላቸውን የደን ችግኞች ለሱማሌ ክልል በስጦታ ማበርከቱንም አቶ ጎጁ ተናግርዋል ፡፡
ዘጋቢ ፡ አብዮት በቀለ ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ከ36 ሚሊዬን ብር በላይ ወጪ የተሰራው የኡማ ባኬ መንገድ ተጠናቆ ተመረቀ
የ2017 የክረምት ወራት የገቢ አሰባሰብና የ2018 ዓ.ም የንግድ ፈቃድ ምዝገባና እድሳት ስራ በአግባቡ ለመስራት መዘጋጀታቸውን በጋሞ ዞን ባለድርሻ አካላት ገለጹ
የክልሉ ኦዲት ግኝት አስመላሽ ኮሚቴ አበረታች ሥራ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ