በረመዳን ወቅት የታየው ትጋትና አንድነት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተመላከተ
1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በዲላ ከተማ በድምቀት ተከብሯል
በበዓሉ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የጌዴኦ ዞን አስተዳዳሪ ዝናብ ወልዴ(ዶ/ር)፥ መስሊሙ ማህበረሰብ በሀገር ደረጃ ለሚሠሩ የልማት ሰራዎች ከመንግሰት ጎን በመቆም የልማትና ሠላም ተምሳሌት እንድትሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው፥ ይህ እሴት፣ ትጋትና አንድነት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች እንዲጠናከሩ አሁን ያለው ሠላም እንዲቀጥል ያሳሰቡት አስተዳዳሪው 1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው በዓሉ የሠላም፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን ተመኝተዋል።
የዲላ ከተማ አሰተዳደር ከንቲባ መስፍን ደምሴ(ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ከተማችንን የሠላም ተማሳሌት እንድትሆን ያደረጋችሁት የመልካም እሴት አስተምሮት ወደ ቀጣይ ትውልድም በማሸጋገር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ ገልፀዋል።
ለሀገር መንግስትና ለትውልድ ግንባታ የሀይማኖት ተቋማት ወሳኝ በመሆናቸው በቀጣይ በልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች በጋራ በመቀናጀት ከተማዋን የልማትና የሠላም ተምሳሌት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል
የዲላ ከተማ አስተዳደር የእስልምና ጉዳዮች ምክርቤት ዋና ሰብሳቢ ኡስታዝ አብድራህማን አብድቁ የረመዳን ፃም ወቅት በእስልምና እምነት አስተምህሮት መነሻ የተቸገሩትን በመርዳትና በመደደጋገፍ፣ ለሠላምም ፈጣሪን በመፀለይ ያሳለፍንበትና የአብሮነትና የመተሳሰብ ዕሴቶቻችን ጎልቶ የታዩበት ነው ብለዋል።
በረመዳን ፃም ወቅት ያሳለፍነውን መልካም እሴቶችቻችን በበዓሉም ወቅትና ከበዓሉም በኋላ ለቀጣዩ ትውልድ እንዲሸጋገር አጠናክረን ሊንሠራ ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ : ፅጌ ደምሴ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችንን
በረመዳን ወቅት የታየው ትጋትና አንድነት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተመላከተ

More Stories
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
መስቀል የድህነት ምልክት መሆኑን የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል ተናገሩ