በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብዝሃ ባህል፣ ታሪክና እሴትን ለመገንባት በተሠሩ ስራዎች በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገለፀ
ይህ የተገለፀው “በባህልና ቱሪዝም እምርታ ለክልላችን ከፍታ” በሚል መሪ ቃል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የሴክተር ጉባኤ በሳጃ ከተማ እየተከናወነ ባለበት ወቅት ነው።
በጉባኤው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብሄረሰቦች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ ገመቹ አረቦ፣ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ፣ የክልሉ ምክር ቤት የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ አባል አቶ እንዳልካቸው ጌታቸው፣ የክልሉ የአመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብላቱ፣ የየም ዞን የመንግስት ተጠሪና የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብርሀም ዝናብ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በጉባኤው የ2018 ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2019 ጠቋሚ ዕቅድ ዋና ዋና ግቦች ቀርበው ውይይት እየተደረ ነው።
ዘጋቢ፡ ፉኣድ አብደላ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ በመንገድ መሠረተ ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሰኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አሰታወቀ
ሳውላ ከተማን ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ምቹ የማድረግ የ5 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ እየተካሄደ ነው
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቱሪዝም ሀብቶችን በማልማትና ሰላምን በማጽናት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል