የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የህግና አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ገመገመ
በግማሽ አመቱ የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሀገራዊ የመዋቅር ማሻሻያ ተከትሎ ተቋማትን የማደራጀት ተግባራት ላይ በትኩረት በተሰሩ ስራዎች ለውጥ መመዝገቡን በሪፖርት ተመላክቷል።
በመንግስት ሰራተኞች ዘንድ የሚነሱ የቅጥር፣ የዝውውርና ምደባ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል አሰራር ተዘርግቶ እየተሰራ መሆኑን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ሐልጋዬ ጂሎ አስረድተዋል።
ሀገር አቀፍ የትምህርት ማስረጃን የማጥራት ተግባራት በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ያሳሰቡት የቋሚ ኮሚቴ አባላት፥ ሳይመዘኑ የሚሻገሩ የመንግስት ሰራተኞች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ መምጣት እልባት የሚሻ ጉዳይ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል።
የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ የሚነሳው በስፋት የሚነሳው የመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ አተገባበር ያለበትን ደረጃ ቋሚ ኮሚቴው በዝርዝር ተመልክቷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሐልጋዬ ጂሎ፥ ከቋሚ ኮሚቴ ለተነሳው ጥያቄና አስተያየት ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፥ በተቋሙ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎችን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።
ከመንግስት ሰራተኞች የሚነሱ ቅሬታዎችን በአግባቡ ምላሽ ለመስጠት በአስተዳደር ፍ/ቤት ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት በቅርቡ ወደ ሙሉ ትግበራ ይገባል ሲሉ አቶ ሐልጋዬ ጂሎ አብራርተዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የህግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዱንጋ ናኩዋ በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት፥ የመረጃ አያያዝ ስርዓት በማዘመንና በማደራጀት እስከ ታችኛው መዋቅር በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ሐሰተኛ ማስረጃዎችን በማጥራት ማጠናከር ያስፈልጋል ያሉት የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢው፥ የመንግስት ሰራተኞች ለሚያነሱት ቅሬታ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ: ተስፋዬ ወ/ማሪያም

More Stories
በክልሉ የሚገኙ ነዋሪዎችን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥራ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለጹ
የእናቶችንና ጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ በሚደረጉ ጥረቶች ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር (ዶ/ር ) እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ምርቃትና የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስረዓት እየተካሄደ ይገኛል