የጉራጌ ክትፎ ባህልና እውቀትን በዩኒስኮ የሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ በተካሄደው ጥናት ዙሪያ በወልቂጤ ከተማ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል
በመድረኩ የኢፌዲሪ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው፣ የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሙዚየምና የምርምር ዘርፍ ዋና ዳይሬከተር አቶ ኤልያስ ሽኩር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህል ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን፣ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል እና የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር (ጉልባማ) አመራሮች፣ የፌደራል፣ የክልል፣ የሁለቱም የጉራጌ ዞኖች የወረዳና የከተማ አስተዳደር የስራ ሀላፊዎችን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመታደም ላይ ናቸው።
የጉራጌ ባህል፣ ታሪክና ቋንቋን በማልማት፣ በመንከባከብና በማስተዋወቅ ከአካባቢው አልፈው በአለምአቀፍ ደረጃ እንዲተዋወቁ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል።
በተለይም የጉራጌ ባህላዊ ክትፎ፣ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) በአለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ መሆኑም ተመላክቷል።
የጉራጌ የባህል እሴቶችን ይበልጥ በማጉላት የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን፣ ከኢፌዲሪ ባህልና ቱሪዝም፣ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ልዩ ልዩ የጥናትና ምርምር ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፡ ሪድዋን ሰፋ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
ዲግሪው “ወረቀት ብቻ ሳይሆን፣ የሀገር ተስፋና የትውልድ ኃላፊነት ነው” – አፈወርቅ ካሱ (ፕ/ር)
በክልሉ የተጀመሩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የድጋፍና ክትትል ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ገለጹ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የግብርና ስራዎችን ተመለከተ