የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አራት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን ተወያይቶ አፀደቀ
ሀዋሳ: ጥር 26/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤ በሁለተኛ ቀኑ አራት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ ተቀብሎ አፅድቋል።
በዚህ መሠረት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ገቢ ግብር አዋጅ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የጫት ኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ባህላዊ ፍርድ ቤቶችን ለማቋቋም እና እውቅና ለመስጠት የወጣ ረቂቅ አዋጅ የሚሉት መሆናቸዉ ተመልክቷል።
ዘጋቢ: ዘላለም ተስፋዬ

More Stories
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄዎች በዘላቂነት እንዲመለሱ ከየትኛውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኧሌ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ገለፀ
መንግስት የደን ጭፍጨፋን በመከላከል የአየር ሚዛንን ለመጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ እስታውቀ
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ እንዲያስችል ዞኑ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ