የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበለትን የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም በሙሉ ድምፅ ተቀብሎ አፀደቀ
ሀዋሳ: ጥር 25/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤ በሁለተኛ ቀኑ የመስተዳድር ምክር ቤትን የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም በሙሉ ድምፅ ተቀብሎ አፅድቋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የበጀት አመቱን የ6 ወራት የመስተዳድር ምክር ቤት እቅድ አፈፃፀም ያቀረቡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው፥ የክልሉን የመልማት አቅም በማገናዘብ በሁለም መስክ የተጀመረው እድገት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።
በክልሉ ያለው የህዝብ ተሳትፎ የሚደነቅ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ በቀጣይ ይህን ተሳትፎ ክልሉን የብልፅግና ተምሳሌት በማድረግ ሊሰራ እንደሚገባ አመላክተዋል።
በሁሉም የልማት ዘርፎች ላይ አዳዲስ ሀሳቦችንና ስልቶችን በመተግበር በሀገራዊ የለውጥ ጉዞ የቤተሰብ ብልፅግናን በማረጋገጥ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ፣ የሌማት ትሩፋትን ማጠናከር፣ በትምህርት፣ በማአጤማ፣ ትርፍ በማምረትና ቁጠባን ማጎልበት ወደ ኢንቨስትመንት መቀየር ላይ በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል።
ከዚህ በተጓዳኝ ክልሉን የተሞክሮ ማዕከል ለማድረግ በሁሉም መስክ ደረጃ ያለው ስታንዳርድ አውጥቶ መተግበር እንደሚያስፈልግ ገልፀው፥ ከዚህ በተጓዳኝ ክልሉን የተረጋጋ፣ ሰላማዊ ክልል በመፍጠር የሸቀጣሸቀጥና የተቀላጠፈ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና ብሎም የሰዎች ያለስጋት ዝውውር እንዲኖር ምቹ ስነምህዳር ሊኖር እንደሚገባ አመላክተዋል።

More Stories
በክልሉ የሚገኙ ነዋሪዎችን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥራ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለጹ
የእናቶችንና ጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ በሚደረጉ ጥረቶች ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር (ዶ/ር ) እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ምርቃትና የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስረዓት እየተካሄደ ይገኛል