በትምህርት ሴክተር እየገጠመ ያለውን ችግር ለመፍታት የትምህርት አመራር ሪፎርም ማድረግ እንደሚያስፈልግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ
ቢሮው “ሪፎርሙ ይዞ የሚመጣውን ብቃትን፣ ትጋትንና ስነ-ምግባርን ለማሻሻል” በሚል መሪ ሀሳብ በትምህርት ቤት አመራር ሪፎርም ጥናት ግኝቶች እና የአፈጻጸም ረቂቅ መመሪያዎች ላይ ግብዓት ለመሰብሰብ ያለመ ስልጠና በአርባምንጭ እያካሄደ ይገኛል።
ሪፎርም ብቃትን፣ ትጋትንና ስነ-ምግባርን ለማሻሻል ጥረት የሚደረግበት ይህ የምክክር መድረክ ከዚህ በፊት ከሚሰጠው ስልጠና ለየት ያለ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመምህራን ትምህርት አመራር ዘርፍ ኃላፊ ታምራት ይገዙ (ዶ/ር) ጠቁመዋል።
በትምህርት ሴክተር እየገጠመ ያለውን ችግር ለመፍታት የትምህርት አመራር ሪፎርም ማስፈለጉን ዶክተር ታምራት ገልጸው፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት ጥናት ሲካሄድ መቆየቱን አስታውሰዋል።
በትምህርት ቤት አመራር በተደረጉ ሪፎርም ጥናት ግኝቶችንና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ እንዲሁም ሪፎርሙን መሠረት ባደረገ መልኩ የተዘጋጁ ረቂቅ መመሪያዎች ላይ ግብዓት ለመሰብሰብ ያለመ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል።
በክልሉ ከመምህራን እና ትምህርት ቤት አመራር ጋር የተያያዙ መመሪያዎች መኖራቸውን ዶ/ር ታምራት ተናግረው፤ አዲሱ የትምህርት ላይ ስልጠና (CPD) ማዕቀፍ ላይ ተጨማሪ ግብዓት የማካተት ተግባር እንዳለ አስቀምጠዋል።
በተጠናው ጥናት መነሻ በትምህርት ቤት መምህራን እና አመራር ላይ እየተካሄደ ያለው ሪፎርም የአንድን ትምህርት ቤት ውጤታማነትን የሚወስን በመሆኑ ሚናውን ለመወጣት በሀሳብ ማዳበር የሚያስፈልግ መሆኑን በክልሉ ትምህርት ቢሮ የመምህራን እና ትምህርት አመራር ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክር አቶ አለማየሁ አንጃ ገለጸዋል።
የተማሪዎችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ በአስተሳሰብ፣ በአመለካከትና በክህሎት የበለጸገ ዜጋ ያስፈልጋል ሲሉ አክለዋል።
የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በመምህራን እና ትምህርት አመራር አደረጃጀት ላይ መሥራት እንደሚገባ ከተሳታፊዎች መካከል በወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ የመምህራን እና ትምሀርት አመራር ልማት ቡድን መሪ አቶ ኢሳይያስ ኃይሉ እና በጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ የመምህራን፣ የትምህርት አመራር እና ሠራተኞች አስተዳደር ቡድን መሪ ወ/ሮ ብዙአየሁ ተረፈ ተናግረዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር ዋና ፀሐፊ አቶ ጌታቸው ካሳ፤ የሪፎርም ሥራው የትምህርት አመራር ችግርን የሚፈታ መሆኑን በአስተያየታቸው ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡ ሰለሞን አላሶ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
በትምህርት ሴክተር እየገጠመ ያለውን ችግር ለመፍታት የትምህርት አመራር ሪፎርም ማድረግ እንደሚያስፈልግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ

More Stories
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄዎች በዘላቂነት እንዲመለሱ ከየትኛውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኧሌ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ገለፀ
መንግስት የደን ጭፍጨፋን በመከላከል የአየር ሚዛንን ለመጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ እስታውቀ
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ እንዲያስችል ዞኑ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ