በባህር ዛፍ የተያዙ ለም መሬቶችን የምግብ ዋስትናን ሊያረጋግጡ በሚችሉ ሰብሎች መተካት መጀመሩ የሚበረታታ መሆኑ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ጥር 22/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) አርሶ አደሩ በተፈጠረለት ግንዛቤ ታግዞ በባህር ዛፍ የተያዙ ለም መሬቶችን የምግብ ዋስትናን ሊያረጋግጡ በሚችሉ ሰብሎች መተካት መጀመሩ የሚበረታታ መሆኑን በሀዲያ ዞን የምዕረብ ሶሮ ወረደ ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ።
ለ25 ተከታታይ ቀናት የሚዘልቀው የዘንድሮ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በወረዳው 2ኛ አቃማ ቀበሌ በሁራ ንዑስ ተፋሰስ በይፋ ተጀምሯል።
አርሶ አደር ደሳለኝ ሌንጃሞ፣ ታምራት ቀልብሶ እና ወ/ሮ አደነች አሾሬ በተፋሰስ ልማት ስራ ማስጀመሪያ መርሃግብር ላይ በነቂስ ወጥቶ ሲሰሩ አግኝተን ያነጋገርናቸው አርሶ አደሮች ሲሆኑ፥ የአከባቢው የመሬት አቀማመጥ ተደፍታማ መሆኑን የሚናገሩት አርሶ አደሮቹ፥ ከዚህ ቀደም መሬታቸው በጎርፍ ተጠርጎ በመወሰዱ የምርታማነት ችግር ይገጥማቸው እንደነበራ አስታውሰዋል።
ይሁንጂ በተፋሰስ ልማት የአፈርና የውሃ ጥበቃ ስራ ከተጀመረ ወዲህም በምርትም ይሁን በአፈር ለምነት አስደሳች ለውጦች መታየቱን ተናግረዋል።
በወረዳው የግብርና ጽ/ቤት ምክልት እና የተፈጥሮ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍቅሩ አሻሞ፥ የአፈርና ውሃና ጥበቃ ስራ የሁሉም አካላትን የነቃ ተሳትፎ የሚጠይቅ እንደሆነ በመግለፅ የተፋሰስ ልማቱ ከመጀመሩ አስቀድሞ የግንዛቤ ስራ በስፋት መሰራቱን አመላክተዋል።
አቶ ፍቅሩ አያይዘውም በሚቀጥሉት ተከታታይ 25 ቀናት በሚተገበረው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ላይ 1ሺህ 410 ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን፥ በዚህ 19ሺህ 485 የህብረተሰብ ክፍሎች እንሚሳተፉ ጠቁመዋል።
የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተረፈ ደመቀ አርሶ አደሩ በተፈጠረለት ግንዛቤ ታግዞ በባህር ዛፍ የተያያዙ ለም መሬቶችን የምግብ ዋስትናን ሊያረጋግጡ በሚችሉ ሰብሎች መተካት መጀመሩ የሚበረታታ ነው ብለዋል።
በወረዳው 2ኛ አቃማ ቀበሌ በሁራ ንዑስ ተፋሰስ የተጀመረው የአፋርና ውሃ ጥበቃ ስራ በ12 ንዑስ ተፋሰሶች የሚቀጥል መሆኑን ጠቁመው፥ በዚሁ ንዑስ ተፋሰስ ብቻ 251 ሄክር መሬት እንደሚለማ አስታውቀዋል።
የተጀመረው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል የቅንጅት ስራዎች ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉት ያመላከቱት አቶ ተረፈ፥ አርሶ አደሩ “ከተረጂነት ወደ ምርታማነት” ለመሸጋገር በሚደረገው ርብርብ መትጋት እንዳለበትም አሳስበዋል።
ዘጋቢ፡ አለቃል ደስታ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
በክልሉ የሚገኙ ነዋሪዎችን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥራ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለጹ
የእናቶችንና ጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ በሚደረጉ ጥረቶች ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር (ዶ/ር ) እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ምርቃትና የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስረዓት እየተካሄደ ይገኛል