ባለፉት ስድስት ወራት ከ7 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዲላ ከተማ ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ
የዲላ ከተማ ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ እርሳሱ አሰፋ፤ ከተማው በርካታ ምርት የሚመረትበትና የንግድ ማዕከል ቢሆንም ከዚህ ቀደም ገቢን ከመሰብሰብ አኳያ ጠንካራ እንዳልነበር አንስተዋል።
ይሁን እንጂ ችግሩን ለመፍታት በተሠራው ሥራ አፈፃፀሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እንደሚገኝ የገለጹት ኃላፊው፤ ዘንድሮ በግማሽ በጀት ዓመቱ ብቻ ከአምናው ሙሉ ዓመት የተሻለ ገቢ መሰብሰቡን ነው ያስረዱት።
ባለሙያዎች ከተጣለባቸው ኃላፊነት አንፃር ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንዲሠሩ ማድረግ፣ ሁሉም የአመራር አካላት የገቢ ሥራን በባለቤትነት እንዲደግፍ ማድረግ፣ ህገወጥ የገቢ ስወራ ላይ ያለውን ቁጥጥር ማጥበቅ፣ መንግሥት ያወጣዉን አዋጅ በጥብቅ ዲሲፕሊን ተፈፃሚ እንዲሆን ማድረግና የመሳሰሉት ከተሠሩ ሥራዎች ለአብነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።
በበጀት ዓመቱ በመደበኛና ማዘጋጃ ቤት 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ በግማሽ ዓመቱ 7 መቶ 15 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ነው አቶ እርሳሱ ያስረዱት።
ዘጋቢ፡ አማኑኤል ትዕግስቱ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
ባለፉት ስድስት ወራት ከ7 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዲላ ከተማ ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ

More Stories
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
መስቀል የድህነት ምልክት መሆኑን የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል ተናገሩ