በተጀመረው የተፋሰስ ዘመቻ ሥነ ህይወታዊና ሥነ አካላዊ የአፈርና ውሃ ጥበቃን በማጠናከር የአረንጓዴ አሻራችንን ራዕይ መደገፍ እነደሚገባ ተገለጸ
ለሚቀጥሉት 30 ቀናት በሚቆየው የተፋሰስ ዘመቻ በባስኬቶ ዞን ዳብጻ ዳልቂንሳ ቀበሌ በይፋ ተጀምሯል።
የባስኬቶ ዞን ግብርና መምሪያ ኋላፊ ዶ/ር ኤፍሬም ገረሱ ከከፍታ ቦታዎች አንስቶ የአፈርና ውሃ እቀባ ሥራዎችን መሥራት፤ የተራቆቱ አካባቢዎችንም ከልሎ ለማልማት ሰፊ ዕቅድ መያዙን ገልጸዋል።
በዘንድሮው የተፋሰስ ልማት በ38 ንዑስ ተፋሰሶች ተለይተው የሚለሙ ሲሆን፥ 44ሺ የሰው ሃይ በማደራጀት 1 ሺህ 600 ኪሎ ሜትር ልዩ ልዩ የአፈርና ውሃ እቀባ ዘዴዎች የሚከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይ የጠጴዛማ እርከን ላይ ትኩረት በመሥጠት ለሴቶችና ወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ለማመቻቸት ይሰራል ብለዋል።
ከተፋሰስ ሥራ ጎን ለጎን ለመደበኛው የበልግ እርሻ ሥራ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ሁሉም የእርሻ ማሳዎች መታረሳቸውንና ሙሉ ፓኬጅ ግበዓት አጠቃቀም ልዩ ትኩረት ይሻል ብለዋል።
የላስካ የዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተመሥገን አዘነ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተፋሰስ ስራ ካለው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አኳያ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ለአካባቢ ጥበቃ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሳሙኤል ደሳለኝ ከዚህ ቀደም በለሙ ተፋሰሶች ላይ የአታክልትና ፍራፍሬ ልማት በትኩረት ማልማት እንደሚገባ ገልጸው የተጀመረው የተፋሰስ ልማት በሁሉም የዞኑ አካባቢዎች ለሚቀጥሉት ተከታታይ 30 ቀናት የሚቆይ መሆኑን አስረድተዋል።
የአፈርን ለምነት በማጥፋት በአካባቢው አጠቃላይ ሥነ ምህዳር ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ የሚገኘውን የባህር ዛፍ ተክል ሙሉ በሙሉ ለምግብነት በሚውሉ ሰብሎች መቀየር ለነገ የማይባል ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል።
በተፋሰስ ሥራ ማስጀመሪያው የተሳተፉ አርሷደሮች በሰጡት አስተያየት ከዚህ ቀደም በተሠራው የተፋሰስ ሥራ የታየውን ለውጥ በተግባር በማረጋገጣቸው በቀጣይ በቂ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ዘጋቢ: አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
በከምባታ ዞን ሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርአት (E-LMIS) ምዝገባ በይፋ መጀመሩን የከተማው ኢንተርፕራይዝና ሥራ ዕድል ፈጠራ ጽህፈት ቤት አስታወቀ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሆሳዕና ከተማ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በተከሰተው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ተደረገ
ህብረተሰቡ የኤሌክትሪክ መስመሮችን ጨምሮ ለእሳት አደጋ መንስኤ የሚሆኑ የመጠቀሚያ ዕቃዎችን በጥንቃቄ በመጠቀም በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት መከላከል እንደሚገባ ተገለጸ