የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠበቅና ምርታማነትን ለማረጋገጥ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ጥር 18/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠበቅና ምርታማነትን ለማረጋገጥ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራን ማጠናከር እንደሚገባ የአሪ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ።
የ2018 ዓ.ም ዞናዊ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ “በጥናት የተረጋገጠ ዕምቅ የመልማት አቅም ለእምርታዊ ብልፅግናችን” በሚል መሪ ቃል የ 30 ቀናት የተፋሰስ ልማት ሥራ በጋዘር ከተማ አስተዳደር በይፋ ተጀምሯል።
የተፈጥሮ ሀብትን በመጠበቅ ምርታማነትን ለማሳደግ ማህበረሰቡ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራን ባህሉ ሊያደርግ እንደሚገባ የንቅናቄ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኣሪ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አፌዶ ወርቁ፥ በዞኑ 131 ሺህ ሕዝብ በላይ በማሳተፍ 11 ሺህ ሄክታር መሬት እንደሚለማ ገልፀዋል።
የኣሪ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ጉራልቅ ይዥማልቅ በበኩላቸው በቀጣይ 30 ቀናት በስነአካላዊና ሥነሕይወታዊ የተፋሰስ ሥራዎች የዞኑ ዕምቅ የመልማት አቅምን ለእምርታዊ ብልፅግና ለማዋል ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል።
የጋዘር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በለጠ ማጎ እና የደቡብ አሪ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገብሬ ባይስጅ በጋራ እንደገለፁት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለውን የተፋሰስ ልማት ሕብረተሰቡ በሁሉም አከባቢዎች በነቂስ ወጥተው እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ከዚህ በፊት በተሠሩ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት ማግኘታቸውን የአከባቢው አርሶአደሮች ጠቅሰው ለዘላቂነቱ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
በመርሃ ግብሩ የሐይማኖት አባቶች፣ የጎሳ መሪዎች፣ ባላባቶች፣ የክልል የዞን የወረዳና ከተማ አስተዳደር አመራሮች ፣ የወርልድ ቭዥን አስተባባሪ እና የግብርናው ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የአርባምንጭ ማረሚያ ተቋም የህብረ ብሔራዊነት ማሳያ እና የምርታማ ዜጋ ማፍሪያ ተቋም ነው – ኮሚሽነር ብርቱካን መንግስቱ
በተጀመረው የተፋሰስ ዘመቻ ሥነ ህይወታዊና ሥነ አካላዊ የአፈርና ውሃ ጥበቃን በማጠናከር የአረንጓዴ አሻራችንን ራዕይ መደገፍ እነደሚገባ ተገለጸ
በህዝባዊ አንድነት የተጀመሩት የልማት ስራዎች ቀጣይነት እንዲኖረው ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል