የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ግዛቸው ዋሌራ እና ሌሎች የቋሚ ኮሚቴው አባላት በተገኙበት የክልሉን መንግስት ጤና ቢሮ የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ግማሽ አመት እቅድ አፈፃፀም ገምግመዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ እና ሌሎች የማናጅመንት አባላት በተገኙበት የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ግማሽ አመት አፈፃፀም ለቋሚ ኮሚቴው ዝርዝር ሪፖርት ቀርቧል።
ቋሚ ኮሚቴውም በቀረበው ዝርዝር ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት አካሂዷል።
በ2018 የመጀመሪያ ግማሽ አመት የተጣሉ ዋና ዋና ግቦችን ለማሳካት ማህበረሰቡን ያሳተፈ መጠነ ሰፊ ርብርብ በአብዛኛዎቹ ተግባራት ላይ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉ ተጠቁሟል።
የግንባታ በጀት ዕጥረት መኖር፣ በጤና አገልግሎት ሽፋንና ተጠቃሚነት ላይ ልዩነቶች መታየት፣ የመድሀኒትና የህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት መቆራረጥ፣ የጤና አመራር ስርአትን የማስፈፀም አቅምና የአመለካከት ውስንነት መኖር በአፈፃፀሙ ሂደት የተለዩ ዋና ዋና ተግዳሮቶች መሆናቸው ተመላክቷል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ግዛቸው ዋሌራ እንደተግዳሮት የተነሱትን በመቅረፍ በጥንካሬ የታዩ ተግባራትን የማስፋትና በጉድለት የተመዘገቡት አፈፃፀሞችን በማረም በቀጣይ ጤናማ አምራች ዜጋን ለማፍራት እንዲተጉ ጠይቀዋል።
ዘጋቢ፡ ቴዎድሮስ ወርቅነህ

More Stories
በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ተገቢውን ትኩረት መስጠትና ተግቶ በመስራት ከድህነት መውጣት ይገባል – ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
ኢትዮጵያን ለዘመናት ከቆየችበት ቁስል ለማላቀቅ ባለፉት የለውጥ አመታት በርካታ ፖለቲካዊ ተግባራት ማከናወኑን መቻሉ ተገለጸ
ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎችን በመስራታቸው ዘርፈ ብዙ ጠቄሜታ ማግኘታቸውን የአርባምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኮሌጅ ተማሪዎችና መምህራን ገለፁ