በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሱ የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከል ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ጥር 14/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሱ የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከል ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የቀቤና ልዩ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
ጽ/ቤቱ የ2018 በጀት አመት የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል፡፡
የቀቤና ልዩ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈቲያ ሱልጣን በዚህ ወቅት እንደገለፁት በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሱ የወንጀል ድርጊቶችን አስቀድሞ ለመከላከል ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የሴቶች አደረጃጀቶችን በማጠናከር በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ያላቸውን ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በተሰሩ ስራዎች የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል ነው ያሉት፡፡
የመድረኩ ዋና አላማ በበጀት አመቱ ባለፉት 6 ወራት የነበሩ ጥንካሬዎችንና ውስንነቶችን በመለየት በቀጣይ የህፃናት ደህንነትን ለማስጠበቅና የሴቶችን ሁለተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን አስታውቀዋል።
በዘርፉ ውጤታማ ስራ እየሰሩ የሚገኙ አደረጃጀቶችና ተቋማት ተሞክሮ ለሌሎችም ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመው፥ በልዩ ወረዳው በየደረጃው በሚከናወኑ የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት የሴቶችና ህፃናት ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የመድረኩ ተሳታፊዎች ተናግረዋል ፡፡
ለነዚህ ስራዎች ውጤታማነትም መላው ማህበረሰብና ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የሴቶች አደረጃጀቶች፣ ከየሴክተሩ የተወጣጡ የስርዓተ ፆታ ኦፊሰሮችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ፡፡
ዘጋቢ: ጅላሉ ፈድሉ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄዎች በዘላቂነት እንዲመለሱ ከየትኛውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኧሌ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ገለፀ
መንግስት የደን ጭፍጨፋን በመከላከል የአየር ሚዛንን ለመጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ እስታውቀ
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ እንዲያስችል ዞኑ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ