ተዓማኒና ወቅቱን የጠበቀ መረጃ ለሀገራዊ ሁለንተናዊ ዕድገት ፋይዳው የጎላ መሆኑን በኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት የሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታወቀ
ጽ/ቤቱ በክልሉ ከተለያዩ አካባቢዎች ለተውጣጡ ከ1 ሺ 4 መቶ በላይ ለሚሆኑ ለዘርፉ ባለሙያዎችና ተቆጣጣሪዎች በዲላ ዩኒቨርሲቲ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።
ሰልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት በኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት የሀዋሳ ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አሰጋሽ አሰፋ፤ ተዓማኒና ወቅቱን የጠበቀ መረጃ ለሀገራዊ ሁለተናዊ ዕድገት ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።
ስልጠናው ለኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ መስክ ሰራተኞች በክልል ደረጃ የሚሰጥ መሆኑን ጠቁመው፤ ሠልጣኞች ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በተግባር እንዲወጡ ጠይቀዋል።
መረጃ የሀገር ሀብት በመሆኑ መረጃ ሰጪዎች ተክክለኛ መረጃ መስጠትና መረጃ ሰብሳቢዎችም በአግባቡ ትክክለኛ መረጃ በመሰብሰብ ለሀገር ተጠቃሚነት ሊሰሩ እንደሚገባም ሥራ አስፈፃሚዋ አሳስበዋል።
በስልጠና ላይ ተገኝተው እንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተወካይ ዶ/ር ሀብታሙ ተመስገን፤ በሀገሪቱ ያሉ እውነታዎችንና የኢኮኖሚ ተግዳሮቶችን ለይቶ መረጃን መሰብሰብ ጠንካራ ኢኮኖሚን ለመገንባት ይረዳል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት የሀዋሳ ቅርንጫፍ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ዋና አስተባባሪ አቶ ኦልሰን አወል፤ እንደ ክልል በዲላና ወንዶገነት ሥልጠና ማዕከላት 1 ሺ 4 መቶ በላይ የዘርፉ ባለሙያዎችና ተቆጣጣሪዎች በስልጠናው እንደሚሳተፉ ገልፀዋል።
አንደአስተባባሪው ገለፃ፤ መረጃው በሀገሪቱ የተለያዩ አምራች ድርጅቶች ተጨባጭ መረጃ ለማሰባሰብ የሚረዳ ከመሆንም ባሻገር የኢኮኖሚ ድርጅቶች ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችል ነው።
ስለጠናው ለሚቀጥሉት 10 ቀናት የሚዘልቅ መሆኑን የጠቆሙት ስራ አስኪያጁ፤ ጥራት ያለውን መረጃ ማሰባሰብ የሚያስችል እውቀት መቅሰሚያ መድረክ እንደመሆኑ ሠልጣኞችም ሆኑ አሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸው ወቅት የድርሻቸውን እንዲወጡ አቶ ኦልሰን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፡ ዘርሁን ሹፌር – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
በቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የትምህርት ተቋማት ጥራት አስተዳደር ሥርዓት ተጀመረ
በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሱ የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከል ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ
ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለው ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ቀጣይነት እንዲኖረው የአምራች ድርጅቶች ቆጠረ እና ምዝገባ ጉልህ ሚና እንደሚኖር በኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት የሆሳዕና ቅርንጫፍ አስታወቀ