ሀዋሳ፡ ጥር 13/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ በክልሉ ለሚገኙ አቃቢያነ ህግ በተሻሻለው የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017 የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
የክልሉ ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ጤናሁን ጨርቆስ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት በተለይም የተሻሻለው አዲሱ የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017 ቀደም ሲል በፍትህ ስርዓት ላይ እንደጉድለት የሚነሱ ችግሮችን የሚቀርፍና በደረጃ አወሳሰንና እርከን ላይ መሻሻልን ያስቀመጠ እንደሆነ አብራርተዋል።
የዘርፉ ባለሙያዎች ከወቅቱ ጋር የሚሄድ አሰራር እየተከተሉ አዋጆችን በተገቢው በመረዳት መፈፀም እንደሚገባ ያስረዱት ምክትል ቢሮ ኃላፊው በአቃቢያነ ህግ ስነ ምግባር ደንብ መሠረት መተግበር እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
አዲሱ የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017 ቀደም ሲል በነበረው አዋጅ ውስጥ ጉድለት የነበሩ ጉዳዮችን የሚቀርፍና በህብረተሰቡ ዘንድ አስተማሪ አይደሉም የሚባሉ ውሳኔዎችን የሚያሻሽል እንደሆነ አስረድተዋል።
አክለውም ባለሙያዎች ባገኙት ዕውቀት ታግዘው ውጤታማ ስራዎችን ማከናወን ይገባል ብለዋል።
የተከለሰው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ትክክለኛነት እና ወጥነትን በሚያረጋግጥ አግባብ ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
ሕዝቡ ከየትኛውም የወንጀል ስጋት ነጻ እንዲሆንና ወንጀል የፈጸሙም ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ያደርጋል ብለዋል።
ሁሉም ኃላፊነቱን ከተወጣ የፍትሕ ሥርዓቱን በሕዝብ የታመነ እና የሕግ የበላይነት የተረጋገጠበት ማድረግ ስለሚቻል ይህ እውን እንዲሆን ሁሉም የፍትሕ አካላት ኃላፊነት እንዳለባቸው አንስተዋል።
ዘጋቢ፡ አይናለም ሰለሞን – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
መስቀል የድህነት ምልክት መሆኑን የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል ተናገሩ