የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ጂንካ ቅርንጫፍ የ6 ወር አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በጅንካ ከተማ ተካሂዷል፡፡
የደቡብ ሬዲዮና ተሌቪዥን ድርጅት ጅንካ ቅርንጫፍ ስራ ከጀመረበት ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ አማርኛን ጨምሮ በ12 ቋንቋዎች ለህብረተሰቡ አስተማሪና አዝናኝ የሆኑ ዜናና ፕሮግራሞችን በተለያዩ ዘዴዎች ተደራሽ ሲደርግ ቆይቷል።
ቅርንጫፍ ጣብያው ለኣሪ፣ ለደቡብ ኦሞ እና ለአሌ ዞኖች የሚዲያ ሽፋን እየሰጠም ይገኛል።
የአፈፃፀም ግምገማ መድረኩን የመሩት የቅርንጫፍ ጣቢያዉ ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኜ ጥላሁን፤ በበጀት ዓመቱ 6 ወራት በይዘት ዘርፍ፣ አስተዳደር፣ በግዢና ፋይናንስ እንዲሁም በማስታወቂያና ገበያ ልማት እና በሚዲያ ቴክኖሎጂ በተከናወኑ ተግባራት የቅርንጫፍ ጣቢያዉ አፈፃፀም አበረታች መሆኑን ገልፀዉ በቀሪ ወራት እያንዳንዱ ስራ ክፍልና ባለሙያ በተሰማሩበት የስራ መስክ ለተሻለ ዉጤት ሊሰሩ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በአየር ሰአት ሽያጭ በሬዲዮ ማስታወቂያና ከስፖንሰር ሺፕ የተሻለ ገቢ መሠብሰብ መቻሉንም በሪፖርቱ ተመላክቷል።
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በ2018 በጀት ዓመት መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና ተቋማት ጋር በነበረው ትብብር የሚዲያ ባለሙያዎች አቅም ማጎልበቻ ስልጠና መሠጠቱን ስራ አስኪያጁ አብራርተዋል።
ይሁን እንጂ በተቋሙ በቂ ስርጭት ለማድረግ የማሰራጫ መሳሪያዎች ብልሽት እና በጀት ማነቆ እንደሆነባቸዉ የገለፁት ስራ አስኪያጁ፤ ችግሩን ለመፍታት ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በአፈፃፀም ግምገማ መድረኩ ላይ የተገኙ ባለሙያዎች በበኩላቸው ለስራ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች እንዲሟላላቸዉ ጠይቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ራሔል አብራሃም – ከጅንካ ጣቢያችን

More Stories
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄዎች በዘላቂነት እንዲመለሱ ከየትኛውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኧሌ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ገለፀ
መንግስት የደን ጭፍጨፋን በመከላከል የአየር ሚዛንን ለመጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ እስታውቀ
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ እንዲያስችል ዞኑ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ