ሀዋሳ፡ ጥር 04/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማርበርግ ቫይረስ በሽታ ቤተሰቦቻቸውን ካጡ ወገኖች ጎን በመቆም ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደምገባ የክልሉ ጤና አስታወቀ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ በማርበርግ ቫይረስ በሽታ ወላጆቻቸውን ላጡ ህጻናት ማቋቋምያ የሚሆን የቤት ግንባታ ማስጀመርያ መርሃ ግብር ተካሒዷል።
በበጎነትና ቅንነት ሐሳብ ተነሳስተው በበሽታው ወላጆቻቸውን ላጡ ህጻናት ድጋፍ ለማፈላለግ የተሰባሰቡ ቅን ልቦች የማህበረሰብ ተኮር ምላሽ ቡድን መሪ አቶ አስራት ጉንቦ እንደገለጹት፥ በማርበርግ በሸታ እናትና አባታቸውን ያጡ ህጻናትን ለማቋቋም ታስቦ ማህበረሰቡንና በጎ አድራጊ ድርጅቶችና መንግስታዊ አካላትን ሁሉ በማካት ከሰባት ሚልየን ብር በላይ በገንዘብና በአይነት ለማሰባሰብ ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን አስታውቀዋል።
በእስካሁኑ ሒደት በገንዘብና በአይነት ከሁለት ሚልየን አምስት መቶ ሺህ ብር በላይ ማሰባሰብ መቻሉን ጠቁመው፥ በጂንካ ከተማ ሶስት ቦታዎች ለህጻናቱ መቋቋምያ የሚሆን የቤት ግንባታ ማስጀመርያ መርሐ ግብር መከናወኑንና እስከፍጻሜውም ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ለዚህም አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብረሐም አታ እና የጅንካ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ውባለም ገዛኸኝ እንደገለጹት፥ የማርበርግ ቫይረስ በአከባቢው ከተከሰተ ወዲህ ህጻናትን ጭምር ያለ ወላጅ ያስቀረ በመሆኑ መላው ማህበረሰቡና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ለነዚህ ህጻናት የሚሆን ድጋፍ በማሰባሰብ ለዛሬው የቤት ማስጀመርያ መርሐ ግብር ለበቁት የቅን ልቦች ቡድን ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይም ዞኑና ከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ በማድረግ ከጎናቸው እንደሚቆም አስረድተዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንደሻው ሽብሩ በበኩላቸው፥ አስከፊ በሆነው በማርበርግ በሽታ ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናትን ለማቋቋም ታስቦ በቅን ልቦች ጠንሳሽነት የተጀመረው ሁሉ አቀፍ ድጋፍ እጅግ የሚደነቅ መሆኑን አስረድተው፥ በጂንካ ከተማ በሶስት ቦታዎች የተከናወነው የቤት ማስጀመርያ መርሐ ግብር እጅግ አስደሳች እንደሆነና በቀጣይም ለተጎጂ ወገኖች በሚደረገው ማንኛውም ድጋፍ ቢሮው የበኩሉን ሚና እንደምወጣ ተናግረዋል።
በቫይረሱ ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናትና ወገኖችም እንደተናገሩት በደረሰባቸው መሪር ሐዘን በእጅጉ መጎዳታቸውን ጠቁመው፥ እየተደረገላቸው ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ: ተመስገን ሠይፉ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
ስፖርተኞች መልካም ስብእና ተላብሰው ውድድራቸውን እያካሄዱ እንደሚገኙ የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ
የፀረ-ተህዋስያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድን ለመከላከል በሚደረገው አገራዊ ጥረት ውስጥ የሚዲያ ባለሙያዎች ግንባር ቀደም ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ገለጸ
መምህራን የሚገባቸውን ጥቅማ ጥቅምና መብት በማስጠበቅ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር አስታወቀ