3ኛው የጉራጌ ዞን የልዩ ልዩ ስፖርት ሻምፒዮናና የባህል ስፖርት ዉድድር በወልቂጤ ከተማ መካሄዱን ቀጥሏል።
ሰሞኑን የጀመረው የጉራጌ ዞን የልዩ ልዩ ስፖርት ሻምፒዮናና የባህል ስፖርት ውድድር ስፖርተኞች መልካም ስብእና ተላብሰው ውድድራቸውን እያካሄዱ እንደሚገኙ የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትልና የስፖርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አደም ሽኩር ገልጸዋል።
አቶ አደም አክለውም ቀድሞ የተዘጋጀው የውድድሩ መተዳደሪያ ደንብን ተግባራዊ በማድረግ ውድድሮች እየተካሄዱ እንደሚገኝኙ ሲያነሱ፤ በዘንድሮው ሻምፒዮና የሴቶችን ተሳታፊነት ለማሳደግ በተሰራው ስራ ሴቶች በተለያዩ ስፖርት እየሳተፉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
በውድድሩ ዞኑን የሚወክሉ ተተኪ ስፖርተኞች እየተመለመሉበት መሆኑን ያነሱት ሀላፊው፤ ውድድሩ በቀጣይም ብርቱ ፉክክር የሚታይበት መሆኑን አስረድተዋል።
ውድድሩ በተለያዩ የስፖርት አይነቶች በተለያዩ ሜዳዎች እየተከናወኑ መሆኑን ያነሱት ደግሞ በመምሪያው የስፖርት ውድድርና ተሳትፎ ቡድን መሪ አቶ አብድልፈታ ናስር ሲሆኑ በ7 ዘመናዊ እና በ6 ባህላዊ የስፖርት ውድድሮች በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ተወዳዳሪዎችም በፍጹም ስፖርታዊ ጨዋነት ውድድራቸውን እያካሄዱ መሆኑን ያነሱት አቶ አብድልፈታ፤ በቀጣይ ውድድሩ እስኪጠናቀቅ ተግባሩ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመላክተዋል።
ያነጋገርናቸው የውድድሩ ተሳታፊዎች ውድድሩን በጉጉት ሲጠብቁት የነበረ መሆኑን ሲያነሱ ስፖርታዊ ጨዋነት በተሞላበት መልኩ ውድድራቸውን እያከናወኑ እንደሆነ አስረድተዋል።
አመቱን በሙሉ ለውድድሩ ሲዘጋጁ እንደነበር የገለጹልን ተወዳዳሪዎቹ፤ መሰል ውድድሮች መዘጋጀታቸው አቅማቸውን ለማሳየት የሚያግዝ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመላክተዋል።
በአራት ምድብ ተከፍሎ እየተደረገ የሚገኘው የእግር ኳስ ውድድር በትላንትናው ውሎ አንድ ጨዋታ ሲደረግ ወልቂጤ ከተማ አስተዳደርን ከእምድብር ከተማ አስተዳደር ሲያገናኝ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል።
በቴኳንዶ የITF ውድድር ፍጻሜውን ሲያገኝ ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የዋንጫ ባለቤት ሲሆን አበሽጌ ወረዳ ሁለተኛ በመሆን ሲያጠናቅ እዣ ወረዳ በሶስተኛነት አጠናቋል።
በሻምፒዮናው የቮሊቮል ውድድር ላይ በወንዶች ጾታ አበሽጌ ከእዣ ያገናኘው ጨዋታ አበሽጌ ሶስት ለዜሮ በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
ልዩ ልዩ ሻምፒዮናው በዛሬው እለትም ሲቀጥል በእግር ኳስ 3:00 እንደጋኝ ከ ጉመር 5:00 ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከ እኖር 7:00 ጉንችሬ ከአገና ከተማ አስተዳደር 9:00 እዣ ከ ምሁር አክሊል የሚጫወቱ ይሆናል።
ዘጋቢ፡ ዳዊት ዳበራ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
የፀረ-ተህዋስያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድን ለመከላከል በሚደረገው አገራዊ ጥረት ውስጥ የሚዲያ ባለሙያዎች ግንባር ቀደም ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ገለጸ
መምህራን የሚገባቸውን ጥቅማ ጥቅምና መብት በማስጠበቅ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር አስታወቀ
የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራትን ለማፋጠን ግብር ከፋዩ የሚጠበቅበትን ታክስ በወቅቱና በታማኝነት መክፈል እንዳለበት ተገለጸ