አርሰናል በአስቶንቪላ ተሸነፈ
በ15ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ከሜዳው ውጪ ከአስቶንቪላ ጋር የተጫወተው የሊጉ መሪ አርሰናል ሽንፈትን አስተናግዷል።
እጅግ እልህ አስጨራሽ የነበረው እና 30 ሙከራዎች የተደረጉበት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በአስቶንቫላ 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።
ለአስቶንቪላ ወሳኝ የማሸነፊያ ጎሎችን ማቲ ካሽ እና ኢሚሊያኖ ቡንዲያ አስገኝተዋል።
አርሰናልን ከሽንፈት ያልታደገችውን ጎል ደግሞ ሊያንድሮ ትሮሳርድ አስቆጥሯል።
ሊያንድሮ ትሮሳርድ በፕሪሚዬር ሊጉ 50ኛ ጎሉን አስቆጥሯል።
ፖላንዳዊው የቀኝ መስመር ተከላካይ ማቲ ካሽ በዚህ ዓመት 3ኛ የሊግ ጎሉን አስቆጥሯል።
አርሰናል በሁሉም ውድድሮች ከ18 ጨዋታዎች በኋላ ሽንፈትን አስተናግዷል።
አስቶንቪላ በሊጉ 5ኛ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል።
አስቶንቪላ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 30 በማድረስ ከመሪው አርሰናል በ3 ነጥብ አንሶ 2ኛ ደረጃን ይዟል።
በሊጉ 2ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርሰናል በ33 ነጥብ የደረጃ ሰንጠረዡን እየመራ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ማንቸስተር ሲቲ በዚህ አጨዋወት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም”ፖል ሜርሰን
ኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ህዝብ ለህዝብ የሚያስተሳስርና አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ