ሊቨርፑል ዌስትሃምን አሸነፈ
በ13ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ሊቨርፑል ከሜዳው ውጪ ዌስትሃም ዩናይትድን በማሸነፍ በሊጉ ከሁለት ተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል።
በለንደን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የመርሲሳይዱ ክለብ መዶሻዎቹን 2 ለ 0 በማሸነፍ ወሳኝ ድል አስመዝግቧል።
የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ጎሎች አሌግዛንደር ኢሳቅ እና ኮዲ ጋግፖ አስገኝተዋል።
በጨዋታው በዌስትሃም ዩናይትድ በኩል ሉካስ ፓኩዌታ በሁለት የማስጠንቀቂያ ቢጫ ቀይ ካርድ ተመልክቶ ከሜዳ ወጥቷል።
አሌግዛንደር ኢሳቅ በሊቨርፑል የመጀመሪያ የፕሪሚዬር ሊግ ጎሉን አስቆጥሯል።
ሊቨርፑል ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 21 በማድረስ 8ኛ ደረጃን ይዟል።
8ኛ የሊግ ሽንፈቱን ያስተናገደው ዌስትሃም በአንፃሩ በ11 ነጥብ 17ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በሌሎች ጨዋታዎች ብራይተን ከሜዳው ውጪ ኖቲንግሃም ፎረስትን 2 ለ 0 በሆነ ተመሳሳይ ውጤት ረቷል።
አስቶንቪላ ደግሞ በሜዳው ቡባካር ካማራ ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል ዎልቭስን በማሸነፍ 3ኛ ደረጃን መያዝ ችሏል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ማንቸስተር ሲቲ በዚህ አጨዋወት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም”ፖል ሜርሰን
ኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ህዝብ ለህዝብ የሚያስተሳስርና አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ