አሌክሳንደር አርኖልድ ለሁለት ወራት ከሜዳ የሚያርቀውን ጉዳት አስተናገደ
የሪያል ማድሪዱ የቀኝ መስመር ተከላካይ ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ ለሁለት ወራት ከሜዳ የሚያርቀውን ጉዳት ማስተናገዱ ተገልጿል።
እንግሊዛዊው ተጫዋች ጉዳት ያስተናገደው ትናንት ምሽት ሪያል ማድሪድ ከሜዳው ውጪ አትሌቲክ ቢልባኦን 3ለ0 በረታበት ጨዋታ ነው።
ተጫዋቹ በ53ኛው ደቂቃ ተቀይሮ ከሜዳ ከወጣ በኋላ በተደረገለት ምርመራ የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው ክለቡ አሳውቋል።
ጉዳቱን ተከትሎ አሌክሳንደር አርኖልድ ቢያንስ ለሁለት ወራት ከሜዳ ሊርቅ እንደሚችል ማርካ አስነብቧል።
በእነዚህ ጊዜያት ውስጥም 10 የሚሆኑ ጨዋታዎች ሊያመልጡት እንደሚችል ተመላክቷል።
የ27 ዓመቱ ተጫዋች አሌክሳንደር አርኖልድ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት የልጅነት ክለቡን ሊቨርፑልን ለቆ ወደ ሪያል ማድሪድ መዛወሩ የሚታወስ ነው።
ሎስብላንኮዎቹን ከተቀላቀለ ወዲህ ለ3ኛ ጊዜ ነው ጉዳት ያስተናገደው።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ማንቸስተር ሲቲ በዚህ አጨዋወት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም”ፖል ሜርሰን
ኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ህዝብ ለህዝብ የሚያስተሳስርና አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ