ዊሊያም ሳሊባ ከለንደን ደርቢው ጨዋታ ውጪ ሆነ
ፈረንሳዊው የመሀል ስፍራ ተከላካይ ዊሊያም ሳሊባ አርሰናል በሰሜን ለንደን ደርቢ ከቼልሲ ጋር ከሚያደርገው ወሳኝ ጨዋታ ውጪ ሆኗል።
ዊሊያም ሳሊባ በልምምድ ወቅት ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ከጨዋታው ውጪ መሆኑ ተገልጿል።
ይህንን ተከትሎ አዳዲስ ፈራሚዎቹ ክርስቲያን ሞስኬራ እና ፒዬሮ ሂንካፒዬ ለመጀመሪያ ጊዜ ተጣምረው ይጫወታሉ።
በሌላ በኩል ቪክቶር ግዮኬሬሽ ከበርንሌይ ጨዋታ በኋላ እንዲሁም ጋብርኤል ጄሱስ ከጥር ወር በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በተጠባባቂ ወንበር ላይ ተቀምጠው ጨዋታውን ይጀምራሉ።
በቼልሲም በኩል ከሁለት ወራት በኋላ ወደ ሜዳ የተመለሰው ኮል ፓልመር ከተጠባባቂ ወንበር ተነስቶ ጨዋታውን ያደርጋል።
ለ212ኛ ጊዜ የሚካሄደው የለንደን ደርቢ ጨዋታ ከምሽቱ 1 ሰዓት ከ30 ጀምሮ በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም ይደረጋል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ማንቸስተር ሲቲ በዚህ አጨዋወት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም”ፖል ሜርሰን
ኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ህዝብ ለህዝብ የሚያስተሳስርና አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ