ከፖል ስኮልስ በላይ አሲስት ማድረግ የቻለው ብሩኖ ፈርናንዴዝ
ብሩኖ ፈርናንዴዝ በማንቸስተር ዩናይትድ ከታሪካዊው ተጫዋች ፖል ስኮልስ የበለጠ በፕሪሚዬር ሊጉ ጎል የሆኑ የመጨረሻ ኳሶችን ማቀበል ችሏል።
ብሩኖ ፈርንዴዝ በዛሬው ዕለት ክለቡ ማንቸስተር ዩናይትድ ወደ ደቡብ ለንደን አምርቶ ክርስቲያል ፓላስን ከመመራት ተነስቶ 2 ለ 1 በረታበት ጨዋታ ሁለቱንም የማሸነፊያ ጎሎች አመቻችቶ አቀብሏል።
ተጫዋቹ የዛሬዎቹን አሲስቶች ጨምሮ 56 የመጨረሻ ኳሶች በፕሪሚዬር ሊጉ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
ይህንንም ተከትሎ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከፖል ስኮልስ በላይ በመሆን በማንቸስተር ዩናይትድ በርካታ ጎል የሆኑ ኳሶችን በማቀበል 4ኛው ተጫዋች ሆኗል።
ለ19 ዓመታት በማንቸስተር ዩናይትድ ቤት ተጫውቶ ያሳለፈው ፖል ስኮልስ በ499 የሊግ ጨዋታዎች 55 ግብ የሆኑ የመጨረሻ ኳሶችን ነው ማቀበል የቻለው።
ዌልሳዊው ሪያን ጊግስ 162 ጊዜ አሲስት በማድረግ በማንቸስተር ዩናይትድ ቀዳሚው ተጫዋች ነው።
ዋይን ሮኒ 93 አመቻችቶ በማቀበል ተከታዩን ደረጃ ሲይዝ ዴቪድ ቤካም በ80 ኳሶች 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ማንቸስተር ሲቲ በዚህ አጨዋወት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም”ፖል ሜርሰን
ኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ህዝብ ለህዝብ የሚያስተሳስርና አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ