ማንቸስተር ዩናይትድ ወደ አሸናፊነት ተመለሰ

ማንቸስተር ዩናይትድ ወደ አሸናፊነት ተመለሰ

ሀዋሳ፡ ሕዳር 21/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በ13ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ማንቸስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ክርስቲያል ፓላስን በመርታት ከ3 ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል።

በሴልሀርስት ፓርክ ስታዲየም ማንቸስተር ዩናይትድ ከመመራት ተነስቶ 2ለ1 አሸንፏል።

በጨዋታው ፊሊፕ ማቴታ በ36ኛው ደቂቃ በፍፁም ቅጣት ምት ጎል አስቆጥሮ ፓላስን ቀዳሚ ማድረግ ችሎ ነበር።

ይሁን እንጂ ጆሿ ዚርክዜ እና ማሰን ማውንት በሁለተኛው አጋማሽ ማንቸስተር ዩናይትድን አሸናፊ ያደረጉ ሁለት ጎሎችን አስገኝተዋል።

ጆሿ ዚርክዜ ከ24 የፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎች በኋላ ጎል አስቆጥሯል።

ብሩኖ ፈርናንዴዝ በማንቸስተር ዩናይትድ ቤት 56 ጎል የሆኑ የመጨረሻ ኳሶችን በፕሪሚዬር ሊጉ አመቻችቶ አቀብሏል።

ማንቸስተር ዩናይትድ በፕሪሚዬር ሊጉ ከአርሰናል ጋር እኩል 10 ጎሎችን ከቆመ ኳስ አስቆጥሯል።

ቀያይ ሰይጣኖች ከ5 ዓመታት በኋላ ክርስቲያል ፓላስን ማሸነፍ ችሏል።

ሉክ ሾው በማንቸስተር ዩናይትድ ማልያ 300ኛ ጨዋታውን በዛሬው ዕለት አከናውኗል።

ክርስቲያል ፓላስ በሜዳው ከ12 ጨዋታዎች በኋላ ሽንፈትን አስተናግዷል።

ማንቸስተር ዩናይትድ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 21 በማድረስ ወደ 6ኛ ደረጃ ከፍ ብሏል።

በሊጉ 3ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ክርስቲያል ፓላስ ደግሞ በ20 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ