አርባምንጭ ከተማ በሸገር ከተማ ተሸነፈ
በ6ኛ ሳምንት የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ አርባምንጭ ከተማ በሸገር ከተማ ተሸንፏል።
ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሸገር ከተማ አዞዎቹን 1ለ0 አሸንፏል።
የሸገር ከተማን የማሸነፊያ ጎል ሄኖክ አዱኛ በፍፁም ቅጣት አስቆጥሯል።
በጨዋታው በአርባምንጭ ከተማ በኩል አካሉ አቱሞ በሁለት ቢጫ ቀይ ካርድ ተመልክቷል።
አርባምንጭ ከተማ በዚህ የውድድር ዓመት 3ኛ የሊግ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
ሁለተኛ ድሉን ያስመዘገበው ሸገር ከተማ ነጥቡን 8 በማድረስ 10ኛ ደረጃን ይዟል።
እስካሁን አንድም የሊግ ጨዋታ ያላሸነፈው አርባምንጭ ከተማ በበኩሉ በ3 ነጥብ 18ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ማንቸስተር ሲቲ በዚህ አጨዋወት ሊጉን ማሸነፍ አይችልም”ፖል ሜርሰን
ኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ህዝብ ለህዝብ የሚያስተሳስርና አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ከ1500 በላይ ኤሊት አትሌቶች የሚሳተፉበት 6ኛው ዙር የኬሮድ የ15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ ተጀመረ