ሀዋሳ ከተማ ወልዋሎን በማሸነፍ ደረጃውን አሻሻለ
በ6ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀዋሳ ከተማ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን በማሸነፍ ደረጃውን አሻሽሏል።
ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደው ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።
ለሀዋሳ ከተማ የማሸነፊያውን ጎል ብሩክ ታደለ በ69ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል።
ሀዋሳ ከተማ በዚህ የውድድር ዓመት 4ኛ የሊግ ድሉን ሲያሳካ ወልዋሎ አዲግራት በአንፃሩ 5ኛ የሊግ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና የሚመራው ሀዋሳ ከተማ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 13 በማድረስ ከመሪው ሲዳማ ቡና በግብ ክፍያ አንሶ 2ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ በበኩሉ አንድ ነጥብ ብቻ ይዞ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌ ላይ ተቀምጧል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ቼልሲ በርንሌይን በማሸነፍ ተከታታይ ድል አስመዘገበ
አርባምንጭ ከተማ በሸገር ከተማ ተሸነፈ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በነጩ ቤተመንግስት ተከስቷል