ቼልሲ በርንሌይን በማሸነፍ ተከታታይ ድል አስመዘገበ
በ12ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ቼልሲ በርንሌይን 2ለ0 በማሸነፍ 3ኛ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል።
በተርፍ ሙር ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ለቼልሲ የማሸነፊያ ግቦችን ፔድሮ ኔቶ እና ኢንዞ ፈርናንዴዝ ከመረብ አሳርፈዋል።
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ከአራት ዓመታት በኋላ 3 ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎችን ጎል ሳይቆጠርበት ማሸነፍ ችሏል።
ቼልሲ በሁሉም ውድድሮች ባለፉት 5 ተከታታይ ጨዋታዎች አልተሸነፈም።
ቼልሲ ማሸነፉን ተከትሎ በ23 ነጥብ 2ኛ ደረጃን ይዟል።
8ኛ የሊግ ሽንፈቱን ያስተናገደው በርንሌይ በአንፃሩ በ10 ነጥብ 17ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ

More Stories
አርባምንጭ ከተማ በሸገር ከተማ ተሸነፈ
ሀዋሳ ከተማ ወልዋሎን በማሸነፍ ደረጃውን አሻሻለ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በነጩ ቤተመንግስት ተከስቷል