በወላይታ ዞን አረካ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የተሻለ ውጤት መመዝገቡ ተገለፀ
የአረካ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ተካሂዷል።
ተግባራትን ስኬታማ ለማድረግ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ መቆየቱን የከተማው ከንቲባ ኢንጂነር ጥበቡ ሳሙኤል ገልጸዋል።
በከተማው በ1ኛው ሩብ አመት በሁለንተናዊ መስመር የተመዘገቡ እና ከምክር ቤቱ የተነሱ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ያቀረቡትን ሪፖርተር መነሻ በማድረግ በጥንካሬ እና በጉድለት የተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የከተማው ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ በላይሽ ጡናሞ፤ መንግታዊ ሥራዎች መንግስት ያስቀመጠውን አሰራር ተከትለው እንዲሰሩ ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ በመሆኑ ለውጥ መታየቱን አስረድተዋል።
የማህበረሰብ መድኃኒት ቤት ተገንብቶ ወደ ሥራ መግባቱ እንዲሁም የከተማው ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ወረቀት አልባ አገልግሎት በሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ መጀመሩን የምክር ቤቱ አባላት አንስተዋል።
የህፃናት ጉልበት ብዝበዛን ለመከላከል የተሰሩ ሥራዎችን ግንዛቤ ከመፍጠር ባለፈ ህግ በመተላለፍ ወንጀል የተባበሩ አካላትን ተጠያቂ ማድረግ መቻሉን የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጣሊሶ ለገሠ ተናግረዋል።
የፍርድ ቤት አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ያነሱት የአስተዳደር ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ብርሃኑ ሹዬ ናቸው፡፡
ዘጋቢ፡ ድርሻዬ ጋሻው – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
የማታ 1፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም #ደሬቴድ – ቀጥታ ስርጭት #ዜና24 #ዜና #ደቡብቴቪ
የልማት ሥራዎችን ለማሣካት የሚመደብ በጀት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል የጋራ ርብርብ እንደሚጠይቅ ተመላከተ
ሴቶች የቁጠባን ባህል በማዳበር የኢኮኖሚ አቅማቸውን ለማሳደግ በትጋት ሊሠሩ እንደሚገባ ተገለጸ