ማህበሩ ዓላማውን እና የስራ እንቅስቃሴውን በተመለከተ በቦንጋ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ ከፍተኛና መካከለኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይና የአስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘለቀ ወዳጆ፤ ማህበሩ ለህብረተሰቡ የሚያደርገውን ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያጠናክር አመራሩ የበኩሉን አስተዋጽኦ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።
የስራ እንቅስቃሴውን ለመደገፍ የከተማ አስተዳደሩ በቅርቡ የ1.2 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን አቶ ዘለቀ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ጋኖ ገረመው፤ ማህበሩ በኢትዮጵያ ላለፉት 90 ዓመታት በርካታ ሰብአዊ ድጋፎችን ሲያደርግ እንደቆየ ገልጸዋል።
ዋና ዓላማው በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋዎች በሰዎች ላይ የሚደርሱ ችግሮችን ማቃለል ነው ያሉት አቶ ጋኖ፤ እንቅስቃሴውን ይበልጥ ለማጠናከር የሁሉም ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የደም ባንክና የአምቡላንስ አገልግሎቶችን በመስጠት እንዲሁም የመጀመሪያ የነርሶችን ኮሌጅ በመመስረት ጠቃሚ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል።
ማህበሩ እያከናወነ የሚገኘውን የሰብዓዊ ድጋፍ ስራ ለማስቀጠል ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
በስልጠና መድረኩ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሂማኒቴሪያን ዲፕሎማሲና የኮሙኒኬሽን ሰርቪስ ከፍተኛ ባለሙያ በአቶ ንጉሴ አብዬ የስልጠና ሰነድ እየቀረበ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ ትዕግስቱ ጴጥሮስ – ከቦንጋ ጣቢያችን

More Stories
የሕዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ምክር ቤቶች ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ማከናወን እንደሚገባቸው የኮንሶ ዞን ህዝብ ምክር ቤት ገለጸ
የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠበቅ አሳታፊ እና የተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ
ለትምህርት ሥራ ስኬታማነት ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነትና በጋራ መስራት እንዳለባቸው ተገለፀ