የሣውላ ከተማ ህዝብ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን አካሄደ
ሀዋሳ፡ ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሣውላ ከተማ ህዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር መርሃ-ግብር 13ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል።
ጉባኤው የምክር ቤቱንና አስተዳደር ምክር ቤቱን አፈጻጸም ሪፖርቶችን መርምሮ አፅድቋል።
የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ዘሪሁን ትርንጎ ያለፈውን መደበኛ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ በማፀደቅ የምክር ቤቱን የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም አቅርበዋል።
በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ አባላቱ መታረም በሚገባቸውና ቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ በመምከር በሙሉ ድምፅ አፅድቀዋል።
የሳውላ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ንጉሤ መኮንን የ2018 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት የሥራ ክንውን አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
በግብርናው ዘርፍ ላይ የታዩ ክፍተቶች፣ በመድሃኒት አቅርቦትና ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ዙሪያ የአገልግሎት ውስንነቶች እንደነበሩ አውስተው፥ በመማር ማስማር ሂደት የትምህርት ግበዓትና የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል ትኩረት የሚሻ መሆኑ ተመላክቷል።
በከተማ የመሠረተ ልማት ፍትሃዊ ተደራሽነት፣ የህግና ፍትህ አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ክፍተቶች በአፋጣኝ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድባቸው አባላቱ አሳስበዋል።
ህጋዊ የንግድ ሂደትን በማፅናት ከከተማው የሚመነጨውን የውስጥ ገቢ አሟጦ በመሠብሠብ ለልማት ማዋል አሁንም ይበልጥ ትኩረት ይሻል ብለዋል።
ዘጋቢ: አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
በኮሪደር ልማት፣ የመንገድ ግንባታ እና ተያያዥ ስራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ የጠቅላላ ተቋራጮች እና የአገልግሎት ተቋማት ትጋትና ቁርጠኝነት የሚበረታታ መሆኑ ተገለጸ
በሴቶች ላይ የሚደርሱ ማህበራዊ ጫናዎችን ለመከላከል የኢኮኖሚ ባለቤት እንዲሆኑ ለማስቻል ሁሉም ባለድርሻ አካላላት ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተገለፀ
ትምህርት ቤቶች የዉስጥ ገቢያቸዉን በማሳደግ የግብዓት ችግሮችን በመቅረፍ ምቹ የመማር ማስተማር ከባቢን መፍጠር እንዳለባቸዉ ተገለፀ