በሩብ ዓመቱ 3.7 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ ገለጹ

በሩብ ዓመቱ 3.7 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ ገለጹ

ኃላፊዋ ይህን የገለጹት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአስፈፃሚ ተቋማት የሩብ ዓመት የሥራ አፈፃጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ነው፡፡

የመድረኩ የአስፈፃሚ ተቋማት የሩብ ዓመቱ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ ቀርቧል፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ፣ የገቢ አሰባሰብና የመሠረተ ልማት ዘርፍ አፈፃፀሞች ከቀረቡ ሪፖርቶች መካከል ይገኛሉ፡፡

በውድድር ላይ የተመሠረተ የንግድ ሥርዓት ለመፍጠር እየተሰራ ስለመሆኑ የተገለጸ ሲሆን በክልሉ ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን የመከላከል ሥራ እየተሰራ መሆኑ በሪፖርቱ ቀርቧል፡፡

የመንግስት ሠራተኞችን የደመወዝ ጭማሪ ተከትሎ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ የንግድ ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊ ርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል፡፡

በሩብ ዓመቱ የክልሉ የገቢ አሰባሰብ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በመደበኛና በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት 4.2 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 3.7 ቢሊየን ብር መሰብሰቡ ተመላክቷል፡፡

የመንገድ መሠረተ-ልማት ተደራሽነትን በተመለከተ በ2017 ተጀምረው ያልተጠናቀቁ መንገዶችን ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በህብረተሰብ ተሳትፎ መንገዶችን የመሥራትና የመጠገን ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አንስተዋል፡፡

በ“የገጠር ትስስር ለምግብ ዋስትና” ፕሮግራም አዳዲስ የመንገድ ከፈታና በ2017 ተጀምረው ያልተጠናቀቁ የጥገና ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡

በመንገዶች ባለስልጣን የተያዙ መንገዶች በፍጥነት መጠናቀቅ እንዳለባቸው ነው ያመላከቱት፡፡

ዘጋቢ፡ በዳንኤል መኩሪያ – ከቦንጋ ጣቢያችን