በፍራፍሬ እና ቡና ልማት ላይ በመሳተፋቸው ተጠቃሚነታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ አርሶአደሮች ተናገሩ
የመንገድ ዳር የፍራፍሬ ልማት ኢንሼቲቭ ተግባራዊ በማድረግ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
አርሶ አደር ሄራቶ ሹክሬ አበዱሰላም መሀመድ እና ወ/ሮ ውዷ ጀማል በወረዳው የብለዋንጀ ቀበሌ አርሶ አደሮች ናቸው።
በጓሯቸው ባለሙት ፍራፍሬና ቡና ምርት ከቤት ውስጥ የምግብ ፍጆታ አልፎ ለገበያ በማቅረብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እየጨመረ መምጣቱን ገልፀዋል።
በወረዳው በአዲስ መልክ ወደ ተግባር በገባው የመንገድ ዳር የፍራፍሬ ልማት ኢንሼቲቭ የተሰማሩ አርሶ አደሮች በበኩላቸው፤ ከዚህ በፊት በባህር ዛፍ ተሸፍኖ በነበረ መሬታቸው ላይ የሚበላ ፍራፍሬ ለአብነትም ቋሚ ገቢ የሚያስገኙ ፓፓዬ፣ አቦካዶና ሙዝ ከማልማት ጎን ለጎን በአጭር ጊዜ የሚደርሱ ጎመን፣ ቆስጣ፣ ሰላጣ እና ቃሪያ በማልማት በአሁን ሰዓት ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በወረዳው በባህር ዛፍ ተይዞ ከነበረ ከ20 ሄክታር መሬት 16 ሄክታር ያህሉ በመንገድ ዳር የፍራፍሬ ልማት ኢንሼቲቭ እየለማ መሆኑን የገለፁት የሁልባራግ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አወል ጀማል ናቸው።
አርሶ አደሩን ከተለመደው የግብርና ስራ በማላቀቅ በመንገድ ዳር የፍራፍሬ ልማት ኢንሼቲቭ ላይ እንዲሰማራ ለማድረግ የሚያስችል የግንዛቤ ስራ የተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
አሁን ላይ ባህር ዛፍ በተነሳበት ቦታ ፍራፍሬ፣ የጓሮ አትክልትና ስራስር ተክቶ የማልማት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በወረዳው ከዚህ በፊት የሴፍቲኔት ተረጂ የነበሩ አርሶ አደሮች በዘርፉ ተሰማርተው ውጤታማ በመሆን ከተረጂነትና የሰው እጅ ከመጠበቅ ተላቀው የራሳቸውን ገቢ በመፍጠር ተጠቃሚ መሆናቸውን አቶ አወል ተናግረዋል።
በፍራፍሬ እና ቡና ልማት የተሳተፉ አርሶ አደሮችን በመጠቀም የችግኝ አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም በወረዳው ባሉ አራት የችግኝ ጣቢያዎች በማዘጋጀት የማቅረብ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ዘጋቢ: አሚና ጀማል – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
የቃል ኪዳን ቤተሰብ ምስረታ ለዘላቂ ሠላም ግንባታ ጉልህ ፋይዳ መኖሩን የሠላም ሚኒስቴር ገለፀ
የሴቶችና ህፃናት ጥቃት ለመከላከል ቅድሚያ ከራስ መጀመር እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ ገለፁ
በተለያዩ የልማት መስኮች ሴቶችን በማሳተፍ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑ ተመላከተ