ወ/ሮ ሰላማዊት ማሞ የሸካ ዞን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሾሙ
የሸካ ዞን ምክር ቤት 5ኛ ዙር 13ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በዞኑ ቴፒ ከተማ አካሂዷል።
ምክር ቤቱ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በሸካ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ አለሙ አቅራቢነት ወ/ሮ ሰላማዊት ማሞ የሸካ ዞን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው እንዲሾሙ ባቀረቡት መሰረት በምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።
በሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በአቶ አበበ ማሞ አቅራቢነት ሌሎችም ዕጩዎች በአባላቱ ሙሉ ድምፅ ሹመታቸው የፀደቀ ሲሆን ተሿሚዎቹ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው የኃላፊነት ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።
በዚህም መሠረት ምክትል አፈ ጉባኤዋን ጨምሮ
አቶ ተሾመ አስረስ – የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት
አቶ ሙሉዓለም ስለሺ – የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሁም
አቶ ደምስስ አየለ – የማሻ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት በመሆን የተሾሙ ሲሆን በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሀላ ፈፅመዋል።
ዘጋቢ: አስቻለው አየለ – ከማሻ ጣቢያችን

More Stories
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
መስቀል የድህነት ምልክት መሆኑን የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል ተናገሩ