መንግስት ዜጎችን ከድህነት ለማላቀቅ ትላልቅ መሠረተ ልማቶችን እየዘረጋ ከሚያከናዉናቸዉ ተግባራት አንዱ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ቀጥሎ የባህር በር ጉዳይ መሆኑ ለመላ ኢትዮጵያዉያን የህልዉና ጉዳይ ነዉ ሲሉ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የደቡብ ኦሞ ዞን የመንግስት ስራ ኃላፊዎች አሰታወቁ
የአንድ ሀገር ዜጎች ተፈጥሮ የቸራቸዉን ፀጋ አልምተዉ የመጠቀም መብታቸዉን ለማረጋገጥ መንግስት የአንበሳዉን ድርሻ ይወስዳል።
ከዚህ መነሻነት የሀገራችን መንግስትም ዜጎቹን ከድህነት የማላቀቂያዉ መንገድ የተፈጥሮ ሀብትን በአግባቡ አልምቶ ለመጠቀም ትላልቅ እርምጃዎችን እየወሰደ ያለ ሲሆን ኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤትነቷን በሰጥቶ መቀበል መርህ ለማረጋገጥ እየሰራ ነዉ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የደቡብ ኦሞ ዞን ስራ ኃላፊዎችም መንግስት እያቀረበ ያለዉ የባህር በር ጥያቄ ሕዝባዊ መሠረት ያለዉ በመሆኑ እንደ ዞን ለተፈፃሚነቱ እየተጉ እንዳሉ ተናግረዋል።
በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸዉን ከሰጡት የስራ ኃላፊዎች መካከል የዞኑ ፍትህ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ነፃአለም ኪዳነ ማርያም፣ የትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መልካሙ ሽበሺ፣ የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ ተወካይ አቶ መሳይ ብርሐኑ እና ሌሎችን ጨምሮ ከደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ጂንካ ቅርንጫፍ ጣቢያ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ መንግስት ዜጎችን በዘላቂነት ከድህነት ለማላቀቅ ትላልቅ የልማት ዉጥኖችን ጀምሮ እየጨረሰ በመሆኑ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ቀጥሎ የሀገራችን የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ሕዝባዊ መሠረት ያለዉ በመሆኑ መላዉ የዞኑ ማህበረሰብና ኢትዮጵያዉያን ለተፈፃሚነቱ እንተጋለን ብለዋል።
ኃላፊዎቹ አክለዉም፤ የባህር በር ጥያቄያችን ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እያገኘ በመምጣቱ በቅርብ ጊዜ ተፈፃሚ እንደሚሆን እምነታችን ነዉ ሲሉም ተናግረዋል።
እንደ ሀገር የባህር በር ስኬት የወጪና ገቢ ምርቶች ዝዉዉር በማድረግ እየወጣ ያለዉን ከፍተኛ የወደብ ኪራይ የሀገር ሀብትን ከማስቀረቱ ባሻገር በዓለም ላይ ተወዳዳሪነታችንን የሚያረጋግጥ የኢኮኖሚ ገፅታን የሚገነባ እንደሆነም ተመላክቷል።
ዘጋቢ: ወንድማገኝ በቀለ – ከጂንካ ጣቢያችን
መንግስት ዜጎችን ከድህነት ለማላቀቅ ትላልቅ መሠረተ ልማቶችን እየዘረጋ ከሚያከናዉናቸዉ ተግባራት አንዱ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ቀጥሎ የባህር በር ጉዳይ መሆኑ ለመላ ኢትዮጵያዉያን የህልዉና ጉዳይ ነዉ ሲሉ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የደቡብ ኦሞ ዞን የመንግስት ስራ ኃላፊዎች አሰታወቁ

More Stories
የወባ በሽታ ስርጭትን የመከላከልና የመቆጣጠርን ጉዳይ ቀዳሚ ተግባር አድርጎ እየሰራ መሆኑን የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ
አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ተገልጋዩን ለማርካት እየሰራ መሆኑን የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል አስታወቀ
የባስኬቶ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ አመት የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን አካሂዷል