የክልሉ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 24ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል

የክልሉ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 24ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 24ኛ መደበኛ ስብሰባውን በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት በማካሄድ ላይ ይገኛል።

መስተዳድር ምክር ቤቱ በዚሁ በ24ኛ መደበኛ ስብሰባው፡-

የክልሉን መንግስት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም በመገምገማ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ፣ በታችኛው የአስተዳደር እርከን የአስፈጻሚ አካላት የስልጣን እና ተግባር የመዋቅር ማሻሻያ እንዲሁም የቀረቡ የተለያዩ ረቂቅ ደንቦች መርምሮ ማፅደቅን ጨምሮ ሌሎች የካቢኔ ውሳኔ የሚሹ ተያያዥ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት