የወረዳው ሴቶች አዳዲስ አሠራሮችና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ምሳሌ የሚሆኑ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆናቸውን ገለጹ

የወረዳው ሴቶች አዳዲስ አሠራሮችና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ምሳሌ የሚሆኑ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆናቸውን ገለጹ

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የወረዳው ሴቶች አዳዲስ አሠራሮችና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ምሳሌ የሚሆኑ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆናቸውን በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ በልማት ህብረት የተደራጁ ሴቶች ገለፁ፡፡

የወረዳው ሴቶች በልማት ህብረት በመደራጀት ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የወረዳው ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት አስታውቋል።

በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ የአረቅጥ ሸለቆ ቀበሌ የልማት ሕብረት ሰብሳቢ ወ/ሮ ላቀች ልጅገባ እንደገለፁት ለወረዳው ሴቶች የሚመጡ አዳዲስ አሠራሮችና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለሌሎችም ምሳሌ መሆናቸውን ጠቁመው፥ በየዘርፉ ባስመዘገቡት ውጤት ቀበሌው መመረቁን ተናግረዋል፡፡

የግልና የጋራ ቁጠባ በማድረግ ኢኮኖሚያቸውን በማሳደግ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የቀበሌው ነዋሪ ወ/ሮ አምበዛች ቴኒ በበኩላቸው በየወቅቱ በጤና በትምህርትና በግብርና በመወያየት ለችግሮች መፍትሔ እንደሚያበጁና ሁሉም ሴቶች እንዲበቁ እያደረጉ መሆኑን ጠቁመው በጓሮ በመስራት ትልቅ ደረጃ እንደሚደርስ አስረድተዋል።

በመንግሥት የሚደረግላቸውን ድጋፍ በመጠቀም በቀበሌው ፆም የሚያድር መሬት እንዳይኖር የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑን ገልፀዋል።

በወረዳው የባድና ኢጎር ቀበሌ የሳሬም የልማት ሕብረት ሰብሳቢ ወ/ሮ አበበች ካሣ እንደተናገሩት በሕብረት ማልማት ከጀመሩ ጊዜ ጀምሮ በርካታ ለውጦች አምጥተዋል ።

ባለፉት አራት አመታት በተፋሰስ ልማት ጠረጴዛማ እርከን በመስራትና ከ9 ሄክታር በላይ መሬት በማልማት ምርታማ መሆናቸውን ገልፀው የተፈጥሮ ማዳበሪያ በመጠቀም የጓሮ አትክልት ከማሰቸው በማግኘታቸው ከገበያ መግዛት ማቆማቸውን ተናግረዋል።

በመሥራት መለወጥ እንደሚቻል መገንዘባቸውን ወ/ሮ አበበች አክለዋል።

የጉመር ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ሀላፊ ወሮ ዙልፋ ሹምበጅ እንደገለፁት የወረዳው ሴቶች በልማት ህብረት በመደራጀት ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነታቸውን ከፍ ለማድረግ እየተሰራ ነው። በጎልማሶች ትምህርት በጤና በቁጠባና በሌሎችም ዘርፎች እንደሚወያዩ ገልፀው በግብርና በሌማት ቱርፋት በጓሮ አትክልትና ሰፋፊ ማሳዎችን በማልማት ላይ ይገኛሉ።

በየዘርፉ ግንዛቤያቸው እያደገ በመምጣቱ ከምርታማነት ባሻገርም የምግብ ስርአታቸው እየተሻሻለ መሆኑን ወ/ሮ ዙልፋ አስረድተዋል።

ዘጋቢ፡ ሄኖክ ተክሌ – ከወልቂጤ ጣቢያችን