የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታውን ዛሬ ያካሂዳል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታውን ዛሬ ያካሂዳል

በአፍሪካ አህጉር በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ አንድ የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታውን ዛሬ ምሽት ያካሂዳል።

ዋልያዎቹ የመጨረሻ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ከሜዳቸው ውጪ ከቡርኪና ፋሶ ጋር ነው የሚያከናውኑት።

ጨዋታው ዋጋዱጉ በሚገኘው 4 አውት ዋጋዱጉ ስታዲየም ከምሽቱ 4 ሰዓት ጀምሮ የሚያደርግ ይሆናል።

ብሔራዊ ቡድኑ በጨዋታው አረንጓዴ ማልያ፣ ቢጫ ቁምጣ እና ቀይ ካሶተኒ በማድረግ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ተገልጿል።

እንዲሁም ተጋጣሚው የቡርኪና ፋሶ ብሔራዊ ቡድን ደግሞ ሙሉ ነጭ መለያ ለብሶ ወደ ሜዳ ይገባል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኑ በምድቡ እስካሁን ካከናወናቸው 9 ጨዋታዎች መካከል 2 ጨዋታዎችን ያሸነፈ ሲሆን በ3ቱ አቻ ወጥቶ በ4 ጨዋታዎች በመሸነፍ 9 ነጥቦችን ይዞ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ቡርኪናፋሶ በበኩሏ 18 ነጥቦችን በመሰብሰብ ከምድቡ ወደ ዓለም ዋንጫ ማለፏን ያረጋገጠችውን ግብፅን ተከትላ 2ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ